ሀይማኖታዊ ሳንሱር
ዓርብ፣ የካቲት 6 2001ማስታወቂያ
የኢራን አብዮት መሪ አያቶላህ ሆሚኒ ከሀያ ዓመታት በፊት የ “The Satanic verses” ሠይጣናዊ ጥቅሶች መጸሀፍ ደራሲና የመጸሀፉ አሳታሚ በሞት እንዲቀጡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸው ይታወቃል። መጸሀፉ የፈጣሪን እና የነብዩን ስም ስለሚያጎድፍም ማንኛውም ሙስሊም ይህን የሞት ትዕዛዝ በደራሲው ላይ እንዲተገብር አያቶላህ ሆሚኒ ውሳኔ አስተላልፈዋል። ከአረብ የእስልምና ዓለም የተገኙት ፈላስፋ ሳዲቅ አል አዚም አሁን አደገኛ ሁናቴ ውስጥ ሊከታቸው በሚችል መልኩ ለደራሲ ሳልማን ሩሽዲና ለመጸሀፉ መከራከር ይዘዋል።