ሁለት ዛፍ በሁለት ሺህ ብለን?
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 15 2000ማስታወቂያ
የብዝሃ ህይቀት ጥበቃን ለማጠናከር ዓለም ዓቀፍ ጉባኤያት ይካሄዳሉ ስምምነቶችም ይፈረማሉ። ያንን መካፈልና መፈረሙ ብቻዉን በቂ ሊሆን አይችልም፤ ተግባራዊ ርምጃ ሲወሰድ እንጂ።
ዛሬ ዛሬ ተፈጥሮ በሚፈፀምባት አግባብ የሳተ ድርጊት ሳቢያ አመጿን ስታሳይ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ አብረዉ የመሄዳቸዉ ነገር ግድ መሆኑን ማመላከቱ ይመስላል። በአንድ አካባቢ የታሰበ የልማት ተግባር የአካባቢዉን ይዞታ ብሎም በኗሪዎቹ ህይወት ላይ ሊያስከትለዉ የሚችለዉ አሉታዊ ተፅዕኖ ከግምት ሊገባ እንደሚገባዉ ባለሙያዎቹ ደጋግመዉ አንስተዉታል። ያ ግን ሲደረግ አይታይም።