1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቱርኩ ፕሬዚዳንት ጀርመንን ለመጎብኘት በርሊን ገቡ

ዓርብ፣ ኅዳር 7 2016

የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬጄፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጀርመንን ለመጎብኘት መዲና በርሊን ገቡ። የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች የአዉሮጳ ሃገራት በጦርነቱ ያላቸዉ አቋም ከቱርኩ ፕሬዚደንት የተለየ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ወደ በርሊን የመጡት ፕሬዚዳንቱ በተለያዩ ጉዳዮች ከመራሔ መንግሥቱ ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር እና ቱርክ አቻቸዉ ራቺብ ttኢeብ ኤርዶጋን
የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር እና ቱርክ አቻቸዉ ራቺብ ttኢeብ ኤርዶጋን ምስል picture alliance/dpa/Bernd von Jutrczenka

በእስራኤል ሃማስ ጦርነት የቱርክ አቋም ከአዉሮጳ ህብረት እና ከጀርመን የተለየ ነዉ

This browser does not support the audio element.

የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬጄፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጀርመንን ለመጎብኘት መዲና በርሊን ገቡ። ከሦስት ዓመት ወዲህ ኤርዶጋን ወደ ጀርመን ሲመጡ ይህ ለመጀመርያ ጊዜ ነዉ። የእስራኤል እና ሃማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች የአዉሮጳ ሃገራት በጦርነቱ ያላቸዉ አቋም ከቱርኩ ፕሬዚደንት  የተለየ በሆነበት በአሁኑ ወቅት ወደ በርሊን የመጡት ፕሬዚዳንቱ በተለያዩ ጉዳዮች ከመራሔ መንግሥቱ ጋር ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል። የቱርኩ ፕሬዚዳንት የበርሊን ጉብኝትን ተከትሎ በብዙ ፖሊሶች ጥበቃ ከተደረገላቸው በኋላ ከሦስት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓርብ ዕለት ጀርመንን ይጎበኛሉ።  ከሌሎች የፌዴራል ግዛቶችና ከበርሊን የተሰባሰቡ ወደ 1500 የፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ጥበቃ ለማድረግ መሰማራታቸዉም ተገልጿል። እሁድ እለት የጀርመን እና የቱርክ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድኖች ያደርጉታል የተባለዉ የወዳጅነት ጨዋታም ተሰርዟል። የቱርኩ ፕሬዚዳንት በሚገኙባቸዉ በመራሔ መንግሥቱ ቢሮ፤  እና በፕሬዚዳንቱ መቀመጫ በቤሌቩ ቤተ መንግሥት እንዲሁም በቱርክ ኤንባሲ አካባቢ ከፍተኛ የፀጥታ የደህንነት ጥበቃ እየተደረገ መሆኑም ተመልክቷል። የቱርክ ፕሬዚዳንት የጀርመን ጉብኝት አንድምታን በተመለከተ የበርሊኑን ወኪላችንን ይልማ ኃይለሚካኤልን አነጋግረናል።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW