1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ፕሪቶሪያው ግጭት ማቆም ስምምነት የህወሓት መግለጫ

ሐሙስ፣ መጋቢት 5 2016

ህወሓት ከተፈረመ 16 ወራት ያለፈው ውል በከፊል መፈፀሙን፣ በርካታ የስምምነቱ ይዘቶች ደግሞ አሁንም በእንጥልጥል እንዳሉ በውይይቱ መነሳቱን ገልጿል።ህወሓት በስምምነቱ መሰረት ከመከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ሐይሎች አሁንም ከትግራይ አለመውጣቸውን፣ 40 በመቶ የትግራይ ግዛት አሁንም ወደ ክልሉ አስተዳደር እንዳልገባ ማንሳቱን በመግለጫው ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ከህወሃት መሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ከህወሃት መሪዎች ጋር ያደረጉት ውይይት ምስል Ethiopian Broadcasting Corporation

ህወሓት ስለ ፕሪቶሪያው ግጭት ማቆም ስምምነት የህወሓት መግለጫ

This browser does not support the audio element.

በህወሓት እና ፌደራል መንግስቱ መካከል ያሉ የተራራቁ አቋሞች ለማቀራረብ፣ ፖለቲካዊ ውይይት ጨምሮ ቀጣይ መድረኮችን ለማካሄድም ስምምነት ላይ መደረሱን ህወሓት አስታወቀ። ህወሓት በአፍሪካ ሕብረት አዘጋጅነት ባለፈው ሰኞ በአዲስአበባ በተደረገው የፕሪቶርያ ውል አፈፃፀም ግምገማ መድረክ አስመልክቶ ትላንት ባወጣው መግለጫ፥ በውሉ መሰረት ያልተፈፀሙ ያላቸውን ጉዳዮች በመድረኩ ማንሳቱን ገልጿል።

በሳምንቱ መጀመርያ ሰኞ ዕለት በአፍሪካ ሕብረት አዘጋጅነት በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አፈፃፀም ዙርያ የተደረገው ውይይት እና የተነሱ ነጥቦች አስመልክቶ ትላንት መግለጫ ያወጣው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ፥ ከተፈረመ 16 ወራት ያለፈው ውል በከፊል መፈፀሙን፣ በርካታ የስምምነቱ ይዘቶች ደግሞ አሁንም በእንጥልጥል እንዳሉ በውይይቱ መነሳቱን ገልጿል።የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አፈፃፀምና ትችቱ ከአፍሪካ ሕብረት አደራዳሪዎች በተጨማሪ የአሜሪካን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ፣ የኢጋድ ባለስልጣናት እና ሌሎች በተገኙበት መድረክ ህወሓት በስምምነቱ መሰረት ከመከላከያ ሰራዊት ውጭ የሆኑ ሐይሎች አሁንም ከትግራይ አልወጡም፣ 40 በመቶ የትግራይ ግዛት አሁንም ወደ ክልሉ አስተዳደር አልገባም፣ በዚህም አንድ ሚልዮን ገደማ የጦርነቱ ተፈናቃዮች ወደቀዬአቸው አለመመለሳቸውን ማንሳቱ በመግለጫው ጠቁሟል። የአማራ እና አፋር ክልሎች ከስምምነቱ በኋላ

ከዚህ በተጨማሪ የቀድሞ ተዋጊዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት ለመመለስ በሚደረግ ጥረት አስፈላጊ ሀብት ባለመገኘቱ ፈተና መግጠሙ በመድረኩ ማንሳቱን የሚገልፀው ህወሓት ከፌደራል መንግስት የሚጠበቅ የ2014 ዓመተምህረት በጀት አለመለቀቁ ተከትሎ ደግሞ የመንግስት ሰራተኞች እና ጡረተኞች ውዝፍ ክፍያቸውን ሳያገኙ መቅረታቸው እንዲሁም ሌሎች በርካታ ክፍተቶች መፈጠራቸውን ማንሳቱ ጠቁሟል። 

ስለፕሪቶሪያው ስምምነት ናይሮቢ ውስጥ በሁለቱ ወገኖች የተፈረመው ውልምስል Yasuyoshi Chiba/AFP/Getty Images

ህወሓት በትላንትናው መግለጫው በፌደራል መንግስቱ ተወካዮች በኩል ከዚህ በፊት በነበሩ መድረኮች የተነሱ ነጥቦች መልሰው መነሳታቸው አውስቷል። የህወሓት መግለጫ በውይይቱ የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና ህወሓት ለፕሪቶርያው ውል ያላቸውን ተአማኒነት በድጋሚ አረጋግጠዋል የሚል ሲሆን የተራራቁ አቋሞች ለማቀራረብ፣ ፖለቲካዊ ውይይትን ጨምሮ ቀጣይ መድረኮች ለማካሄድም በሁለቱ አካላት በኩል መግባባት ተፈጥሯል በማለት፥ አደራዳሪዎች በሚገኙበት በቀጣይ ጥቂት ወራት ውስጥ ስብሰባ ሊደረግ መስማማት ላይ መደረሱንም አክሎ ገልጿል።የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ግምገማ
በዚሁ የፕሪቶርያ ውል የእስካሁን አፈፃፀም እንዲሁም የህወሓት እና ፌደራል መንግስቱ ግንኙነት ዙርያ አስተያየት እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የሕግ ምሁሩ ተክሊት ገብረመስቀል በሁለቱ የሰላም ውሉ ተፈራራሚዎች መካከል ከቅርብ ግዜ ወዲህ አለመተማመን እየተስተዋለ ነው ሲሉ ይህም አስጊ መሆኑ አንስተዋል።

ሌላው አስተያየት የሰጡን ፖለቲከኛ አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ የፕሪቶርያው ውል በሙሉእነት እንዲፈፀም እና ፈራሚ አካላት ወደሌላ ዙር ግጭት መልሰው እንዳይገቡ አደራዳሪዎች እንዲሁም የዓለምአቀፉ ማሕበረሰብ ጫና ሊፈጥር ይገባል ብለዋል።

ሚሊዮን ኅይለሥላሴ

ኂሩት መለሰ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW