1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ህወሓት በፌደራል መንግሥት ላይ የሰነዘረዉ ክስ

ሚሊዮን ኃይለ-ሥላሴ
ሰኞ፣ መስከረም 5 2018

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የእርስበርስ ግጭት ለመፍጠር ታጣቂዎች እያደራጀ ነው ሲል ህወሓት ከሰሰ። ይህ አካሄድ የሰላም ስምምነት የሚያፈርስ ነው ሲል ህወሓት አክሎ ገልጿል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰረዘው ህወሓት በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች "ብሔራዊ አንድነት ማጠናከር" የተባሉ መድረኮች እያካሄደ ነው።

ህወሓት
ህወሓትምስል፦ Yasuyoshi Chiba/AFP

ህወሓት በፌደራል መንግሥት ላይ የሰነዘረዉ ክስ

This browser does not support the audio element.

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የእርስበርስ ግጭት ለመፍጠር ታጣቂዎች እያደራጀ ነው ሲል ህወሓት ከሰሰ። ይህ አካሄድ የሰላም ስምምነት የሚያፈርስ ነው ሲል ህወሓት አክሎ ገልጿል። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰረዘው ህወሓት በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች "ብሔራዊ አንድነት ማጠናከር" የተባሉ መድረኮች እያካሄደ ነው። 

ትላንት እሁድ ባሰራጨው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስትን የፕሪቶርያ ውል በመጣስ እንዲሁም የእርስበርስ ግጭት ለመቀስቀስ ጥረት በማድረክ የከሰሰው ህወሓት፥ በአንፃሩ የትግራይ ህዝብ ሰላም ለመጠበቅ ብሎ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል ሲል አስታውቋል። ህወሓት በመግለጫው የኢትዮጵያ መንግስት 'ወራሪዎች' ያላቸዉ ሃይሎች ከሉአላዊነት የትግራይ ግዛት ከማስወጣት በተቃራኒ በትግራይ ግጭት ለመፍጠር በአፋር እና በምዕራብ ትግራይ ታጣቂዎች እየመለመለ እና እያስታጠቀ ነው ሲል ከሷል። የቀጠለው የህወሀትና ፌደራል መንግሥት ውዝግብ

ይህ በእንዲህ እንዳለ 'ብሔራዊ አንድነት፡ የትግራይ ህልውና እና አንድነት ለማረጋገጥ' በሚል መሪ ሐሳብ፥ ህወሓት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተለያየ ደረጃ የሚገኙ ካድሬዎቹ በበርካታ የትግራይ ከተሞች እያወያየ ይገኛል። ዛሬም ድረስ የቀጠለው ይህ የህወሓት የንቅናቄ መድረኮች፥ የፓርቲው ከፍተኛ፣ መካከለኛ አመራሮችን ጨምሮ በታችኛው ረድፍ የሚገኙ አባላት ጭምር የሚሳተፉበት ፥ ዓላማውም ብሔራዊ አንድነት በማጠናከር፣ የተጋረጡ የተባሉ አደጋዎችን ለመመከት ያለመ ፖለቲካዊ ትግል ለማድረግ መሆኑም ተገልጿል። በሳምንቱ መጨረሻ በመቐለ በነበረ የህወሓት መድረክ የተሳተፉ 700 የህወሓት ካድሬዎች የኢትዮጵያ መንግስት እየተከተለው ነው ያሉት አካሄድ ተቃውመዋል። ውጥረት ውስጥ የገባው የህወሓት እና የፌዴራል መንግስቱ ግንኙነት

በአቋም መግለጫቸው የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም በፊት ተገዶ የፈረመው የፕሪቶርያ ስምምነት ለመፈፀም ፍቃደኝነት እና ዝግጁነቱ ስለሌለው የውሉ ትልልቅ ይዘቶች እስካሁን ሊፈፀሙ አልቻሉም። ህዝባችን በጠላቶች እጅ እና በመጠልያዎች ሆኖ እያለቀ ነው። በዚህ አላበቃም፥ የትግራይ ህዝብ ለመጉዳት ሲጠቀሙበት የነበረ 'መዝጋት እና ከበባ' በተለያየ መንገድ እየቀጠለ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የትግራይ ህዝብ ወደ እርስበርስ ጦርነት ለማስገባት እና አንድነቱ ለመሸርሸር በአፋር እና ምዕራብ ትግራይ ታጣቂዎች እየመለመሉ፣ እያሰለጠኑ እንዲሁም እያስታጠቁ ነው" ብለዋል። 

ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ክልል የተከፋፈሉት ታጣቂዎች እንቅስቃሴ ያስከተለው ስጋትእየታየ ነው ያሉት አደገኛ ፖለቲካዊ ሁኔታ እንደሚታገሉ እነዚህ የህወሓት አባላት እና አመራሮች ገልፀዋል። "የትግራይ ህዝብ የሚገባው እና ሕገመንግስታዊ ጥያቄ ስላቀረበ፥ አርፋችሁ የምትኖሩ ከሆነ ኑሩ አልያም አርፋችሁ የማትቀመጡ ከሆነ ካለፈው የባሰ ጠቅልለን እናጠፋቹሃለን የሚል ምላሽ እየተሰጠ ነው። ሁኔታዎች እንዲህ ሆነው እያለ ዝምብለን መጠበቅ ስለማንችል፥ የህዝባችን ብሔራዊ ህልውና እና ድህንነት ለማረጋገጥ፥ ብሔራዊ አንድነት በተባለ ዘመቻ የተሰየመ የመመከት ትግላችን ከፍ የሚያደርግ ትግል ውስጥ ለመግባት መግባባት ላይ እና ውሳኔ ላይ ደርሰናል" ሲሉ አክለዋል። በተለያዩ የትግራይ ከተሞች እየተደረጉ ያሉ የህወሓት መድረኮች የተሳታፊዎች የአቋም መግለጫ ተብሎ ተመሳሳይ መልእክቶች ይተላለፍባቸዋል።

በዚህ ህወሓት የሚያቀርበው ክስ እና ወቀሳ ዙርያ ከኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ ለማግኘት ጥረት ያደረግን ሲሆን፥ በኢትዮጵያ ኮምኒኬሽን ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ከበደ ደሲሳ፥ በፕሪቶሪያ ውል አፈፃፀም እንዲሁም ከህወሓት ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ዙርያ በከፍተኛ ባለስልጣናት ጭምር በተደጋጋሚ ማብራሪያ መሰጠቱ በመግለፅ ተጨማሪ ነገር ለመናገር እንደማይሸ ገልፀውልናል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

አዜብ ታደሰ 

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር 

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW