1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህወሓትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ

ሐሙስ፣ ሰኔ 8 2015

ህወሓት በ መግለጫው የፌደራሉ መንግስት የትግራይን ሕገመንግስታዊ ግዛት እንዲያስከብር፣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቋል። የተቋረጠው ሰብአዊ እርዳታም እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል። ህወሓት ያለንበት ምዕራፍ የተወሳሰበ ነው' ያለ ሲሆን፣ ህወሓትን ለማፍረስ እንቅስቃሴ መኖሩንም በመግለጫው አስታውቋል።

Emblem der Tigray People's Libration Font (TPLF)

ህወሓትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔ

This browser does not support the audio element.

ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔን ለማስቀየር ዲፕሎማስያዊ እና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በህወሓት ሕጋዊነት ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ፣ የሰላም ስምምነቱን የሚጎዳ ነው ሲል ፓርቲው ገልጿል።በሌላ በኩል ህወሓት በሚል ስያሜ አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርበው ውድቅ የተደረገባቸው ግለሰቦች ጉዳያቸው ወደ ፍርድቤት እንደሚወስዱ  ተናግረዋል።የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈራረመው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ ህወሓት አስቀድሞ ተሰርዞ የነበረው ሕጋዊ ሰውነቱ ለማስመለስ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማስያዊ ጥረት ማድረጉ እንደሚቀጥል ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በትላንትናው የህወሓት መግለጫ እና በህወሓት እና የምርጫ ቦርድ ውዝግብ ዙርያ አስተያየታቸው ያጋሩን የሕግ ምሁሩ ሙስጠፋ ዓብዱ፣ ህወሓት የምርጫ ቦርድ ውሳኔ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት ለመቀልበስ እንደሚፈልግ ማሳያ ብለውታል። 
ምርጫ ቦርድ በህወሓት የሕጋዊ ሰውነት ዙርያ ያስተላለፈው ውሳኔ በርካታ ክፍተቶች ያሉበት መሆኑ የሚገልፁት የሕግ ሙሁሩ ሙስጠፋ ዓብዱ፥ በመሰረቱም ጉዳዮ የአንድ ፓርቲ እና ምርጫ ቦርድ ውዝግብ አድርጎ መመልከት እንደማይገባ፣ ሊያስከትለው የሚችል ችግርም ታሳቢ በማድረግ ተገቢ ምላሽ ልያገኝ እንደሚያስፈልግ ይናገራሉ። 

ከዚህ ውጭ ህወሓት በትላንትናው መግለጫው የፌደራሉ መንግስት የትግራይ ሕገመንግስታዊ ግዛት እንዲያስከብር፣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ የበኩሉ እንዲወጣ የጠየቀ ሲሆን ወደ ትግራይ የተቋረጠው ሰብአዊ እርዳታም እንዲቀጥል ጥሪ ከቅርቧል። ህወሓት በመግለጫው መጨረሻ 'ያለንበት ምዕራፍ የተወሳሰበ ነው' ያለ ሲሆን፣ ህወሓትን ለማፍረስ እንቅስቃሴ መኖሩንም በመግለጫው አስታውቋል። ይህም በላቀ ጥበብ እንደሚታገለው ገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ህወሓት በሚል ስያሜ አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም የቀረበ የቅድመ እውቅና ጥያቄ አለመቀበሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ዕለት ባሰራጨው ደብዳቤ አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለእነ አቶ ገብረሚካኤል ተስፋይ ብሎ ባሰራጨው ደብዳቤ በህወሓት ስም ለረዥም ግዜ የሚታወቅ ፓርቲ በመኖሩ ይህም በህዝብ ዘንድ መደናገር የሚፈጥር በመሆኑ የቀረበው ጥያቄ አለመቀበሉ አስረድቷል። ጥያቄው ያቀረቡ አካላት የቦርዱ ውሳኔ ይቃወማሉ። ጥያቄው ካቀረቡት መካከል ከሆኑት አቶ ገብረሚካኤል ተስፋይ " እኛ ከታሪክ ጋር መያያዝ የለብንም። እኛ መብታችን ነው የጠየቅነው። ህወሓት የሚባል ፓርቲ ደግሞ የለም ተሰርዟል። ምርጫ ቦርድ ራሱ ነው የሰረዘው። ከተሰረዘ ስሙ ነፃ ነው" የሚሉ ሲሆን፣ መደናገር ይፈጥራል ለሚለው ደግሞ "ለህዝቡ ማስረዳት የኛ ስራ ነው፣ ምርጫ ቦርድ አይመለከተውም" ሲሉ አክለዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ገብረሚካኤል በቀጣይ ጉዳዮን ወደ ፍርድቤት እንደሚወስዱት ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
ታምራት ዲንሳ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW