ህዝባቸውን ለመመገብ አስጊ ሁኔታ ላይ ያሉ ሀገራት
ረቡዕ፣ ነሐሴ 19 2002ማስታወቂያ
ማፕልክሮፍት የተሰኘው የብሪታንያ የአየር ንብረት ተመራማሪ ድርጅት ፤ ለተባበሩት መንግሥታት የምግብ ድርጅት ፤ ስለምግብ ዋስትና ባደረገው ጥናት ፤ ህዝባቸውን በሚገባ መመገብ የሚችሉትን አገሮችና በምግብ እጥረት ለአደጋ ሊጋለጡ የሚችሉትን ዝርዝር በማውጣት አስታውቋል። በጥናቱ መሠረት ፤ የሰሜን አሜሪካ አገሮች፤ ከአውሮፓም ፤ ፊንላንድ፤ እስዊድን፣ ኖርዌይና ደንማርክ ላቅ ያለውን ደረጃ ይዘዋል። ከዚህ አንጻር፤ በሰላም ማጣት የምትታመሰው አፍጋኒስታንና በተለይ 9 የአፍሪቃ አገሮች፤ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ሳቢያ፤ ህዝባቸውን ለመመገብ እንደሚሳናቸውና አሥጊ ደረጃም ላይ እንደሚገኙ ሠንጠረዡ ያስረዳል።
ድልነሣ ጌታነህ
መሳይ መኮንን
አርያም ተክሌ