1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

“ህዝብን የሚገድል ጠላት ነዉ”  የጉጂ አባገዳዎች ህብረት

ዓርብ፣ መስከረም 7 2014

የጉጂ ኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት በደቡባዊ የኦሮሚያ ዞኖች የኦሮሞ ህዝብን አሰቃቂ በሆነ መንገድ ይገድላል ያለዉን የትኛውንም ቡድን በጠላትነት ፈረጀ፡፡ በአከባቢው በተደጋጋሚ በሚስተዋለው የፀጥታ መድፈረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያለፈ የመጣው የሰው ህይወት እያሳሰበን ነው

Karte Sodo Ethiopia ENG

የሰው ህይወትን በሚያጠፉት ላይ በገዳ ስርዓት ውሳኔ ውግዘት ታውጇል

This browser does not support the audio element.

የጉጂ ኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት በደቡባዊ የኦሮሚያ ዞኖች የኦሮሞ ህዝብን አሰቃቂ በሆነ መንገድ ይገድላል ያለዉን የትኛውንም ቡድን በጠላትነት ፈረጀ፡፡ በአከባቢው በተደጋጋሚ በሚስተዋለው የፀጥታ መድፈረስ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያለፈ የመጣው የሰው ህይወት እያሳሰበን ነው ያለዉ የአባገዳዎቹ ህብረት በምዕራብ ጉጂ ዞን ሰሞኑን ባካሄደዉ የሰላም ጉባኤ ነው ውሳኔውን ያስተላለፈዉ፡፡ የኦሮሞ አባገዳዎች ህብረት ሰብሳቢ እና የጉጂ አባገዳ ጅሎ ማንኦ በተለይም ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ከእንግዲህ በአከባቢው የሰው ሕይወትን በሚያጠፉት ላይ በገዳ ስርዓት ውሳኔ ውግዘት ታውጇል ነው ያሉት፡፡

ስዩም ጌቱ 
አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW