1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህይወት ከጎዳና ተዳዳሪነት በኋላ

ሰኞ፣ ሐምሌ 30 2004

እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአለም ዙሪያ ከ80-100 ሚሊዮን ህፃናት እና ወጣቶች በጎዳና ላይ ይኖራሉ። ለጎዳና የሚዳርጓቸው ምክንያቶችም የተለያዩ ናቸው።

Strassenkinder in Teheran Schlagworte: Armut im Iran Rechteeinräumung: Lizenz: frei Quelle: ISNA
ምስል INSA/Arash Khamooshi

የሰው ልጅ እጣ ፋንታ የተለያየ ነው። ፍፁም ባልጠበቁት ሁኔታ በተለያዩ ምክንያቶች ለጎዳና ህይወት የተገደዱ በርካታ ወጣቶች አሁንም ይገኛሉ። 

አቶ ሙላቱ ታፈሰ አዲስ አበባ የሚገኘው የጎዳናው ሁለገብ የመልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት ፕሮግራም ዳሬክተር ናቸው።  ልጆች በምን ምክንያት ለጎዳና እንደተዳረጉ ከተሞክሯቸው ያካፈሉን አለ።

ለምለም 18 አመቷ ነው።  የጥቃት ሰለባ ነች።  ጎዳናው ርዳታ ያደርግላታል። እንደሷ ያሉ ወጣቶች ገና በልጅነታቸው ለጎዳና እንዳይዳረጉ አልያም ከጎዳና ወተው የተሻለ ህይወት እንዲመሰርቱ ጎዳናው ምን አይነት እንቅስቃሴዎች እንደሚያደርግ  አቶ ሙላቱ ታፈሰ አጫውተውናል።

በአለም ዙሪያ ከ80-100 ሚሊዮን ህፃናት እና ወጣቶች በጎዳና ላይ ይኖራሉምስል dpa

 ጎዳናው  ከተመሰረተ 18 አመት ሆኖቷል። እንደ ለምለም ያሉ ወጣት በተለይም ለሴት የጥቃት ሰለባዎች ድርጅቱ የበኩሉን ሲያበረክት ቆይቷል። በአጠቃላይ ከጎዳና ተዳዳሪነት ተላቀው የተሻለ ህይወት የመሰረቱ በሺዎች የሚቆጠሩ አዲስ አበባ ውስጥ ቢኖሩም፤ በከተማው መብራት ስር አሁንም ህፃናት ቆመው እና ተቀምጠው ይታያሉ። ቁጥራቸውን ለማወቅ ከባድ ነው።

ጎዳናው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው ። በብዛትም በርዳታ ገንዘብ ነው የሚንቀሳቀሰው። አቶ ሙላቱ ይህን በሚያደርጉ ጊዜም በርካታ ሆስፒታሎች ነፃ አገልግሎት በመስጠት እንደሚተባበሯቸው ነግረውናል። ዝርዝሩን ከወጣቶች አለም ዝግጅት ያገኙታል።

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW