1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህገ-ወጥነት ሰፍኖበታል የተባለዉ ሸገር ከተማ

ዓርብ፣ ሰኔ 9 2015

በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ከአምስት ወራት በፊት በይፋ የተመሰረተው የሸገር ከተማ አስተዳደር በተያዘው ኣመት አከናወንኩ ባለው በህገወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችን የማጥራት ስራ ከሦስት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ወደ መንግስት መመለሱን አስታወቀ፡፡

Äthiopien Stadt Sheger hat ersten Bürgermeister gewählt
ምስል Seyoum Getu/DW

የሸገር ከተማ መስተዳድር መግለጫ

This browser does not support the audio element.

በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ከአምስት ወራት በፊት በይፋ የተመሰረተው የሸገር ከተማ አስተዳደር በተያዘው ኣመት አከናወንኩ ባለው በህገወጥ መንገድ የተያዙ መሬቶችን የማጥራት ስራ ከሦስት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ወደ መንግስት መመለሱን አስታወቀ፡፡ 
ከተማ አስተዳደሩ ዛሬ መገናኛ ብዙሃንን ጠርቶ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በተያዘው ዓመት የልየታ ስራ የተከናወነበት የከተማ አስተዳደሩ መሬት 78 ሺኅ ሄክታር ያህሉ ብቻ ነው፡፡  ከተማ አስተዳደሩ በመግለጫው በቅርቡ ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ ለተነሳው ውዝግብም ዘላቂ እልባት ላይ መደረሱን ነው ያስገነዘበው፡፡

ከ160 ሺኅ ሄክታር በላይ የቆዳ ስፋት ባለው መሬት ላይ የተመሰረተው ሸገር ከተማ 78 ሺህ ሄክታር ላይ ያረፉ 450 ሺህ ገደማ መሬት ላይ ልየታ አድርጎ ከዚህ ውስጥ በህጋዊ መንገድ ተይዞ የተገኘው 262 ሺኅ ገደማው ብቻ ነው ብሏል፡፡ ከተማ አስተዳደሩ መሬትን በዘመናዊ ፕላን ለማስተዳደር የቅድሚ ትኩረት ሰጥቶት ተንቀሳቅሷል ያሉት የከተማ አስተዳደሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናስር ሁሴን ከ3 ሹኅ ሄክታር የላቀ መሬት ከህገወጥነት ተነትቋል ነው ያሉት በጋዜጣዊ መግለጫው፡፡ “በህገወጥ ግንባተው ላይ ከህገወት ባለሃብት እስከ ደላሎች በሰፊው ተሳትፈዋል፡፡ ከተማ አስተዳደሩን መስርተን ወደዚህ ስንመጣ ከእኩሌታ በላይ የከተማ አስተዳደሩ መሬት ህገወጥነት ሰፈነበት ሆኖ አግኝተነዋል፡፡ በዚህም ከ3031 ሄክታር በላይ መሬት ወደ መንግስት ካዝና እና ለዘርሶአደሩ ተመልሰዋል፡፡”

በከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ ሰፊ ውዝግብ አስነስቶ የነበረው የቤተእምነቶች በተለይም የመስጂዶች ፈረሳ ጋር ተያይዞ የተነሳው አለመግባባት ከቤተእምነቶቹ አመራሮች እና ከአከባቢው ማህበረሰብ ጋር በተደረጉ ተከታታይ ውይይቶች እልባት ተቀምጦለታልም ተብሏል፡፡ “ከከተማው ምስረታ ጀምሮ ለምናደርገው እያንዳንዱ እርምጃ ማህበረሰቡን ስናወያይ ነበር፡፡ ለዚም ነው ውዝግቦቹ ከከተማ አስተዳደሩ ውጪ ሲነሱ የነበረው፡፡ በህገወጥ አሰራር ተገንብተው የፈረሱ ቤተእምነቶች እንደሚታወቀው የሙስሊም ብቻም አልነበረም፡፡ ከዚህ የተነሳ ለምፍትሄው ስንወያይም ውይቱን የጋራ ነው ያደረግነው፡፡ እንደሚታወቀው በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ ከሚገኙ ቤተእምነቶች አብዛኛዎቹ በህገወጥ መንገድ የተገነቡ ናቸው፡፡ አሁን በተሰጠው ዘላቂ መፍትሄው መሰረትም ለቤተእምነቶቹ እንዳስፈላጊነቱ ህጋዊ መሬት እየተዘጋጀላቸው በህገወጥ የተገነባውን ደግሞ እራሳቸው እንዲያነሱት ይሆናል፡፡”

በሸገር ከተማ ውስጥ ከቤተእምነቶቹ በተጨማሪ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የግለሰቦች መኖሪያ ቤቶችም መፍረሳቸው ዓመቱን ሙሉ የውዝግብ ምንጭ ሆኖ ነው የዘለቀው፡፡ በዚህም ሰፊ ማህበራዊ ቀውሶች መከተላቸውን ከሰብዓዊ ተቋማት እስከ ግለሰቦች ድርጊቱን አብጠልጥለውታል፡፡ የሸገር ከተማ ግን ህጋዊነትን የማስፈን ስራ ነው ያከናወንኩ ሲል ይሞግታል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከህገወጥ ቤቶቹ ግንባታ ጀርባ ያሉ ባለስልጣናትስ ምን ያህል ተጠያቂ ሆነው ይሆን በሚል ከዶይቼ ቬለ ጥያቄ የቀረበላቸው አቶ ናስር፤ “ተጣያቂ የሆኑና እየተጠየቁ የሚገኙም አመራሮች አሉ” ብለዋል፡፡ ኃላፊው እክለውም የከተማው በአዲስ መልክ መዋቅር ያስፈለገውም ህገወትነት ተንሰራፍቶበታል ያሉት ከተማ ውስጥ ህጋዊነትን ለማስፈን ነው፡፡

 

ሥዩም ጌቱ 

አዜብ ታደሰ 

ታምራት ዲንሳ 
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW