1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ተቆጣጣሪ ም/ቤት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 30 2014

በአዲስ አበባ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ይገታል የተባለለት ምክር ቤት መመስረቱ ተገለጸ፡፡ በመዲናዋ የምክር ቤቱ ምስረታ የበርካታ የህገወጥ ሰዎች ዝውውር መነሻ እና መዳረሻ ናት በሚባለው አዲስ አበባ የተቀናጀ ስራ በመስራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡

Äthiopien l Addis Ababa, Human Traffic Control Council
ምስል Seyoum Getu/DW

በአዲስ አበባ የህገ-ወጥ ሰዎች ዝውውርን ለመግታት ነው ተብሎአል

This browser does not support the audio element.

በአዲስ አበባ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ይገታል የተባለለት ምክር ቤት መመስረቱ ተገለጸ፡፡ በመዲናዋ የምክር ቤቱ ምስረታ የበርካታ የህገወጥ ሰዎች ዝውውር መነሻ እና መዳረሻ ናት በሚባለው አዲስ አበባ የተቀናጀ ስራ በመስራት የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚረዳ ነው ተብሏል፡፡ በአዲስ አበባ ደረጃ የተመሰረተው ህገወት የሰዎች ዝውውርን የሚከላከለው ምክር ቤት የችግሩ መነሻ ከሚሆኑ ክልሎች ጋር በአብሮነት የሚሰራበት ቋት መኖሩም ነው የተነገረው፡፡ ወ/ሮ ጽዋዬ ሙልነህ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ኃላፊ ናቸው፡፡

ምስል Seyoum Getu/DW

ኃላፊዋ እንደሚሉት አሁን አሁን የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል ለሚባለው ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ከቢሮያቸው ባሻገር በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት ለችግሩ እልባት ለመስጠት ቅንጅታዊ ስራ ማስፈለጉ ለምክር ቤቱ ምስረታ ዋናው ምክኒያት ነው ይላሉ፡፡ አዲስ አበባ ከተማ በአገሪቱ ለበርካታ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ማስተላለፊያነት፣ መነሻ እና መድረሻነት ስሟ ይጠቀሳል፡፡ ይሁንና በርካታ በሰላምና ፀጥታ እጦት ችግር የሚሰቃዩና ለአስከፊ ስደትም ዜጎች የተዳረጉባቸው አከባቢዎች መኖራቸው የምክር ቤቱ በአዲስ አበባ ብቻ መመስረትን እንዴት ችግሩን መፍታት ይቻለዋል የሚል ጥያቄም አንስተንላቸዋል፡፡

ምስል Seyoum Getu/DW

ዛሬ ሰኞ ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የህገወጥ ሰዎች ዝውውር መቆጣጠሪያ ከተለያዩ ተቋማት በተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ሲመሰረት ለተሳታፊዎች ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህገወጥ ሰዎች ዝውውር መከላከል ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ ፈይሳ በበኩላቸው፡፡ በምክር ቤቱ ምስረታ የተለያዩ ጥያቄዎች ከተሳታፊዎች ሲንፀባረቁ፤ በተለይም የስዴት ፍልሰትን ለመግታት ዋናው ተግባር በኢኮኖሚውና ስራ እድል ፈጠራ ላይ በሰፊው መስራት እንደ መፍትሄ ሊቀርብ የሚችል ነው ተብሏል፡፡ የሰዎች ዝውውርን ለመግታት የተቋቋመው አዲሱን ምክር ቤት በኃላፊነት የሚመሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ በዚሁ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።  

 

ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW