1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለህክምና በጉዞ ላይ የነበሩ ሰዎች ታገቱ

ቅዳሜ፣ የካቲት 13 2013

ታማሚውን ጨምሮ ስድስት  ሰዎች በአምቡላንስ ወደ አዲስ አበባ እያቀኑ በነበሩበት ወቅት ሰኞ ዕለት  በግምቢ ወረዳ አባ ሴና በተባለ ጫካ ውስጥ መታገታቸውን  ጠቀመዋል፡፡ ታግተው ከነበሩት መካከል አሽከርካሪውና አንድ የህክምና ባለሙያ  ወደ በቤሰባቸው መቀላቀላቸውን እና ሌሎች ደግሞ እስካሁን አለመገኘታቸውን አመልክተዋል፡፡

Mendi city
ምስል DW/N. Desalegn

ለህክምና በጉዞ ላይ የነበሩ ሰዎች መታገታቸው

This browser does not support the audio element.

ሰኞ ዕለት የካቲት 8/2013 ዓ.ም ከአሶሳ ወደ አዲስ አበባ  ለህኪምና እርዳታ በአምቡላንስ ሲሄዱ የነበሩ ስድስት  ሰዎች በግምቢ ወረዳ አባ-ሴና  በተባለ ስፋራ መታገታቸውን የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ፡፡ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ከማለዲን ሀሊፋ  ታግተው ከነበሩት መካከል ሁለቱ አምልጠው ወደ ቤተሰቦቻቸው መቀላቀላቸውን ለዶይቸቬለ ተናግዋል፡፡ የታገቱትን ለማሰለቀቅም ከጸጥታ ሀይሎች ጋር ተነጋግረው በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተፈለጉ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት አንድ ግለሰብ  በተሽከርካሪ አደጋ በደረሰበት ከፍተኛ ጉዳት ወደ ሆስፒታላቸው መምጣቱን የሚናገሩት የአሶሳ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ከማልአዲን ሀሊፋ ጉዳዩ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ለተሻለ ህክምና ሰኞ ዕለት ወደ አዲስ አበባ መላካቸውን ገልጸዋል፡፡ ታማሚውን ጨምሮ ስድስት  ሰዎች በአምቡላንስ ወደ አዲስ አበባ እያቀኑ በነበሩበት ወቅት ሰኞ ዕለት  በግምቢ ወረዳ አባ ሴና በተባለ ጫካ ውስጥ መታገታቸውን  ጠቀመዋል፡፡ ታግተው ከነበሩት መካከል አሽከርካሪውና አንድ የህክምና ባለሙያ  ወደ በቤሰባቸው መቀላቀላቸውን እና ሌሎች ደግሞ እስካሁን አለመገኘታቸውን አመልክተዋል፡፡ ታግተው ከቀሩት አንዱ ጉዳት የደረሰበት ግለሰብ ሲሆን እንደዚህ ዓይነት ጥቃት በአምቡላንስና ለህክምና በሚንቀሳቀሱ ሰዎች ላይ ደርሶ እንደማያውቅም አክለዋል፡፡ ሌሎች የቀሩ ታጋቾችን ለማስለቀቅም የጸጥታ ሀይሎች ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም መሐመድ በበኩላቸው ባለፈው ሰኞ ማታ ሁለት ሰዓት አካባቢ ሰዎች ስለመታገታቸውና አምቡላስ ስለመቃጠሉ ማረጋገጣቸውን ለዲደቢሊው ተናግረዋል፡፡ ሽፍቶች አምቡላስ በማስቆም ሰዎችን በመሰወር  አምቡላሱን ማቃጠላቸውን  ከአካባው የጸጥታ አካላት መረጃ እንደደረሳቸው እና  የታገቱትን ለማስለቀቅም ጥረት እያደረጉ ቢሆንም እስካሁን ያሉበትን ለማግኘት አልተቻለም ብለዋል፡፡

 ሰኞ ዕለት ከታገቱት መካከል ወደ ቤተሰባቸው የተቀላቀሉት ሁለቱም   የአሶሳ ሆስፒታል ሰራተኞች ሲሆኑ አንዱ ባለፈው ረቡዕ ሌላው ደግሞ ታሞ በነጆ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ ከተደረገለት በኃላ በትናትናው ዕለት ወደ ቤተሰቡ መመለሱን ከሆስፒታሉ ያገነኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW