ለሑጃጆች ቅሬታ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መልስ
ዓርብ፣ ነሐሴ 25 2010ማስታወቂያ
እንደ ድርጅቱ ገላፃ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ለጥቅም ብሎ ሳይሆን ሑጃጆቹ ኢትዮጵያዉያን በመሆናቸዉ ቅድምያ ሰጥቶ ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እያስተናገደ መሆኑን ገልፆአል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የንግድ ክፍል ከፍተኛ ሃላፊ አቶ ቢሻር አወል እንደተናገሩት የሑጃጅ ደንበኖቻችን በሰላም ሄደዉ ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ ጥረት እንደሚደረግና ድርጅቱ ምንም ሌላ አላማ እንደሌለዉ አክለዋል። አቶ ቡሻር አወልን የጂዳ ሳዉዲአረብያ የሚገኘዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ አነጋግሮ ተከታዩዩን ዘገባ ልኮልናል።
ነብዩ ሲራክ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ