ለመንግስት ሠራተኞች የተደረገው የደሞዝ ጭማሪ፣ ስጋቱና ዘላቂው መፍትሔ
እሑድ፣ ነሐሴ 25 2017
የኢትዮጵያ መንግሥት በአዲሱ ዓመት ከመስከረም 2018 ጀምሮ ፣ለመንግሥት ሠራተኞች ፣የደሞዝ ጭማሪእንደሚያደርግ በቅርቡ አሳውቋል። መንግስት 160 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደሚያደርግበት የገለጸው ይህ የደሞዝ ማስተካከያ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩበት ነው። ጭማሪው ተግባራዊ እንዲደርግ ለዓመታት ሲወተውቱና ሲሞግቱ የቆዩ፣ የሠራተኛ እና የሙያ ማኅበራት እንዲሁም ሌሎች አካላት ጥያቄአቸው መልስ በማግኘቱ መደሰታቸውን እየገለጹ ነው።
በአንጻሩ ጭማሪው ሊያስከትል ይችላል የሚሉት የሸቀጦች እና የሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶች እንዲሁም የቤት ኪራይና የመሳሰሉት ዋጋ ንረት ያሳሰባቸው ሠራተኞችም ሆኑ ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ማስተካከያው ትርጉም የለውም እስከማለት ደርሰዋል። መንግስት በበኩሉ በደመወዝ ማስተካከያው ሰበብ ዋጋ በሚጨምሩ ላይ ቁጥጥር እንደሚያደርግና ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።
በሌላ በኩል ጭማሪው ያላካተታቸው በግል እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የተሰማሩ ሠራተኞች የእኛስ ጉዳይ ሲሉ ጥያቄ እያቀረቡ ነው። የጭማሪው ፋይዳእና ስጋቶቹ እንዲሁም ለስጋቶች የሚሰጡ መፍትሔዎች የዛሬው እንወያይ የመነጋገሪያ ነጥቦች ናቸው።
በዚህ ውይይት ላይ አቶ ካሳሁን ፎሎ የኢትዮጵያ የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፈደሬሽን ፕሬዝዳንት ፣ ዶክተር ዮሐንስ በንቲ የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዝዳንት አቶ ሸዋፈራሁ ሽታሁን የፖለቲካዊ-ኤኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኝ እንዲሁም የዶቼቬለ ዘጋቢ ሰሎሞን ሙጬ ተሳትፈዋል።
ሙሉውን ውይይት ለመከታተል ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
ኂሩት መለሰ