1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለስደተኞች አጋርነት ለማሳየት የተደረገ የእግር ጉዞ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 3 2011

በአውሮፓ ያሉ ስደተኞች መብት ሊጠበቅ ይገባል ያሉ ፈረንሳውያን ከጣሊያን የድንበር ከተማ እስከ ፈረንሳይን ከብሪታንያ እስከምታዋስነው ካሌ ድረስ አስር ቀናትን የፈጀ የእግር ጉዞ አድርገዋል።

Calais Flüchtlingslager
ምስል DW/T.Waldyes

ለስደተኞች አጋርነት ለማሳየት የተደረገ የእግር ጉዞ

This browser does not support the audio element.

የፈረንሳይዋ የድንበር ከተማ ካሌ የተሻለ ህይወትን ፍለጋ ወደ እንግሊዝ ለመሻገር ለሚፈልጉ ስደተኞች እንደ መቆያ ጣቢያ ማገልገል ከጀመረች ዓመታት ተቆጥረዋል። የፈረንሳይ መንግስት ስደተኞቹ በየቁጥቋጦው እና ሰወር ያሉ ቦታዎች በየጊዜው የሚመስርቷቸውን መቆያ ሰፈሮች እየተከታተለ ቢያፈርስም ወደዚያ የሚጓዙ ስደተኞችን ግን ማስቆም አልቻለም። የአውሮፓ ሀገራት እነዚህን ስደተኞች በአግባቡ እና ክብራቸውን በጠበቀ መልክ እንዲያስተናግዱ የጠየቁ ሰዎች ከጣሊያን የድንበር ከተማ እስከ ካሌ ድረስ የእግር ጉዞ አድርገዋል።

የፓሪሷ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ የጉዞውን አስተባባሪዎች እና ተሳታፊዎች አነጋግራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ተስፋለም ወልደየስ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW