1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለብሔራዊ ባንክ የገባው ወርቅ አነሰ

ሰኞ፣ ሐምሌ 17 2015

ዘንድሮው ከክልሉ ወደ ብሔራዊ ባንክ የገባው የወርቅ መጠን 478.9 ኪ.ግ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ወደ ብሔራዊ ባንክ ከገባው 2,300 ኪ.ግ ወርቅ ጋር ሲነጻርም የ1821.1 ኪ.ግ ያህል ያነሰ ነው፡፡

Äthiopien | Sitzung des regionalen Staatsrats von Benishangul Gumuz
ምስል Negasa Dessalegn/DW

የቤኒሻንጉል ጉምዝ ምክር ቤት ስብሰባ

This browser does not support the audio element.

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሰላም ጥሪን የተቀበሉ 5889 ታጣቂዎች የተሀድሶ ስልጠና ወስደው በተለያዩ የስራ መስኮች መሰማራቸውን የክልሉ ርዕሰ መስዳድር አቶ አሻድለ ሐሰን አስታወቁ፡፡ የክልሉ መንግስት የጸጥታ ችግሮችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን የተናገሩት ዛሬ መካሄድ በጀመረው የክልሉ ምክር ቤት 16ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ ነው፡፡ 
በክልሉ ከዚህ ቀደም  ጉዳት የደረሰባቸው 107 ትምህርት ቤቶች ተጠግነው ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ዘገባ አመልክተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በጸጥታ ችግር ተፈናቅለው ከነበሩት 475,384 ዜጎች መካከል 449,323 የሚሆነት በአሁኑ ወደ ቀድሞ ቀያቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡ በግጭት ወቅት የወደሙ 10,141 ቤቶች ደግሞ ከለጋሽ ድርጅች ጋር በመተባበር መልሶ መገንባት መቻሉን በቀረበው ዘገባ ተጠቅሷል፡፡
በርካታ ጫናዎች በመቋቋም የክልሉ መንግስት ሰላምን ለማረጋገጥ የተለየ ጥረት ማድረጉን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሐሰን  በገበኤ ላይ ባቀረቡት ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ዘገባ አብራርተዋል፡፡   በክልሉ ከሚንቀሰቃሱ የታጠቁ ቡድኖች ጋር በተደረገው ስምምነት በርካቶች ወደ ህብረሰተቡ መቀላቀላቸውን ተናግረዋል፡፡ ሆኖም በሚያዚያ ወር መጨረሻ  በመተከል ዞን የሰላም ጥሪን ተቀብሎ ወደ ካምፒ ገብቶ ነበር ስለተባሉ ታጣቂዎች  ጉዳይ እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ የወርቅ ምርት ማሳደግን አስመልክቶም በርካታ ተግባራት መከናወኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የወርቅ ምርት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሌላ ስፍራ ይሸጥ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን  ከሚያዚያ ወር ወዲህ በተደረጉ ክትትሎች መጠነኛ መጨመር ማሳየቱን በቀረበው ዘገባ ተመላክተዋል፡፡ ዘንድሮው ከክልሉ ወደ ብሔራዊ ባንክ የገባው የወርቅ መጠን 478.9 ኪ.ግ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ወደ ብሔራዊ ባንክ ከገባው 2,300 ኪ.ግ ወርቅ ጋር ሲነጻርም የ1821.1 ኪ.ግ ያህል ያነሰ ነው፡፡ ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ መጠን ማነስም በህገ ወጥ መንገድ ወርቅ የሚሸጡ ግለሰቦች መበራከት ምክንያት እንደሆነም ተገልጸዋል፡፡በክልሉ በተከሰቱት የሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮ አደጋዎች ተፈናቅለው ከነበሩት 475,384 ዜጎች መካከል በአሁኑ ጊዜ 26 ሺ 61 የሚደርሱት ብቻ በመጠለያ እንደሚገኙ ርዕሰ መስተዳድሩ ካቀረቡት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል፡፡
በክልሉ በግብርና ዘርፍ 26 ሚሊዩን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ተገልጸዋል፡፡ የንግድና ኢንዱስቲሪ፣ የጤና፣ የስራ ዕድል ፈጠራ፣ የመንገድና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች በቀረበው ዘገባ ተካተዋል፡፡ የክልሉ ም/ቤት 16ኛ መደበኛ ጉባኤ ረቡዕ የሚቀጥል ሲሆን በቆይታው የተለያዩ ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 
ነጋሳ ደዳለኝ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
ታምራት ዲንሳ

ምስል Negasa Dessalegn/DW
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW