1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ትምህርትአፍሪቃ

ለትምህርት ጥራት ፈተና መፍትሄው የቱ ጋር ነው?

ሥዩም ጌቱ
ሰኞ፣ መስከረም 5 2018

የትምህርት ሚኒስቴር በትናንትናው እለት የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን ይፋ አድርጓል፡፡ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህን አስመልክቶ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር ለውጥ መምጣቱን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ዋና መስርያ ቤት
የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ዋና መስርያ ቤት ምስል፦ Alemnew Mekonnen/DW

የትምህርት ጥራቱ ፈተና መፍትሄው የቱ ጋር ነው

This browser does not support the audio element.

ለትምህርት ጥራት ፈተና መፍትሄው የቱ ጋር ነው?

የትምህርት ሚኒስቴር በትናንትናው እለት የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን ይፋ አድርጓል፡፡ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ይህን አስመልክቶ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸር ለውጥ መምጣቱን ጠቁመዋል። ከተፈተኑት ተማሪዎች መካከል 8.4 በመቶ ተማሪዎች ብቻ የፈተናው 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የተናገሩት ሚኒስትሩ፤ ከ585 ሺህ 882 ተማሪዎች መካከል 50 በመቶውን የመለሱት 48 ሺህ 900 ግድም ብቻ ናቸው። የትምህርት ባለሙያዎች በዚህ ጉዳይ ከሪፖርት ባሻገር መፍትሄው ላይ አበክሮ መስራት ይገባል እያሉ ነው፡፡  እንወያይ፤ ለኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት ዋና ዋና ፈተናዎች እና መፍትሔዎች

በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ከ600 ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት 591 እንዲሁም በማህበራዊ ሳይንስ 562 ከአምቦ አዳሪ ትምህርት ቤት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡ በተገለጸበት በዘንድሮ የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት፤ በአገር አቀፍ ደረጃ 50 ትምህርት ቤቶች ብቻ ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳለፍ እንደቻሉ ተመልክቷል። ፈተናው ላይ ከተቀመጡት 585 ሺህ 882 ተማሪዎች መካከል 536,962 ማለትም 91.6% ተማሪዎች ከ50 በታች ውጤት ያመጡበት ብሔራዊ ፈተናው 8.4 በመቶው ከግማሽ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ግን ካለፉት ጥቂት ዓመታት የተሻለ አስብሏል።

ለመሆኑ ከተማሪዎቹ ዝቅተኛ ውጤት ማስመዝገብ ጀርባ ያሉት ችግሮች ምንድናቸው? በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ዋጭሌ ወረዳ አስተያየቱን የሰጠን አንድ የ12ኛ ክፍል ተማሪ በተግዳሮትነት የታዘበውን እንዲህ አጋራን፡፡ “ያለው አንደኛውና መሰረታዊ ችግር የመጽሐፍ ስርጭት ችግር ነው፡፡ መምህራንም ብቃት ያላቸው ብቻ ብያንስ በ11ኛ እና 12ኛ ክፍሎች አከባቢ ብመደቡ ውጤቱ በዚህ ደረጃ አይበላሽም ብዬ አስባለሁ፡፡ በተማሪዎችም በኩል ትምህርትን ችላ ብለው እንደ ቲክቶክ እና ፌስቡክ ያሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ብዙ ጊዜ የማትፋት ችግር አለ” በማለት ተግዳሮት ብሎ የተመለከተውን አስረዳ፡፡ «በትግራይ ከመቶ 50 ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል» የትግራይ አስተዳደር

በየዓመቱ እየተመዘገቡ ያሉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እጅጉን አሳሳቢ ነው የሚሉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስርዓተ ትምህርት መምህርና ባለሙያ ፕሮፈሰር ሐመቢሳ ቀነዓ፤ በዘንድሮው ግን ትንሸሽም ቢሆን ብሰራበት የሚል የተስፋ ጭላንጭል ማሳየቱን ጠቁመዋል፡፡ “ጥሩው ነገር የተወሰነች ማሻሻያ ማየት ተችሏል፡፡ ዘንድሮ የተፈተኑ ተማሪዎች ቁጥር ካለፉት ጊዜያት ብያንስም ችግሩ ግን አሁንም መቀጠሉ እሙን ነው፡፡ ይህ ውጤት የሚሳየው መሰረታዊ የሆኑ መንስኤዎቹን አልደረስንባቸውም የሚል ነው፡፡ የመምህራንና ተማሪዎች ተነሻሽነት ለምሳሌ በጉልህ የሚታዩ ችግሮች ናቸው፡፡ ከመንግስት ትምህርት ቤቶች 5 በመቶ ተማሪዎች ብቻ ናቸው ያለፉት መባሉ ልብ ሰባሪ ከመሆኑም አልፎ ችግሩ አልታዬም አልደረስንበትም ማለት ነው” ሲሉ እልባት የሚሹ ችግሮች ሰፊ እንደሆኑ አስረድተዋል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ ምስል፦ Seyoum Getu/DW

ባለሙያው ሊታይ የሚገባ ያሉትን መሰረታዊ የትምህርት ጥራቱን ስብራት መነሻ ስያስረዱም፤ “የትምህርት ባለሙያን ማነሳሳት ነው ቀዳሚው፡፡ መምህራን ከማስተማራቸው በፊት መኖር መቻል አለባቸው፡፡ ምናልባት የአገር ኢኮኖሚ የሚል ምክንያት ልቀርብ ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከልጆቻችን መማር የበለጠ ምን ቅድሚ ልሰጠው የሚገባው ነገር አለ” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ «ወደ ዩንቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር አልቀነሰም»የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ኮራ ጡሸኔ

በየዓመቱ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ፈተና አላለፉም በሚል መገለፃቸውን እንደ አደጋ ነው የምመለከተው የሚሉት የትምህርት ባለሙያው መንግስት ወደ ከፍተኛ ትምህርት ለማይገቡትም የሆነ መግቢ ማዘጋጀት ልያሳስበው የሚገባው ነው ብለዋል፡፡

ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

ዮሃንስ ገብረእግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW