1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ለትግራይ ክልል ወቅታዊ ችግሮች "አፋጣኝ ሰላማዊ መፍትሔዎች"፤የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን

ሰኞ፣ መጋቢት 8 2017

ትግራይ ክልል ውስጥ ያሉ "ፖለቲካዊ አለመግባባቶች በሰብአዊ መብቶች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርሱ አፋጣኝ ሰላማዊ መፍትሔዎችን መውሰድ ያስፈልጋል" ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ።

Äthiopien l Gebäude Ethiopian Human Rights Commission( EHRC)
ምስል፦ Solomon Muchie/DW

የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያወጡት መግለጫ

This browser does not support the audio element.

ለትግራይ ክልል ወቅታዊ ችግሮች "አፋጣኝ ሰላማዊ መፍትሔዎች" እንዲተገበሩ ተጠየቀ

ትግራይ ክልል ውስጥ ያሉ "ፖለቲካዊ አለመግባባቶች በሰብአዊ መብቶች ላይ ተጨማሪ ጉዳት እንዳያደርሱ አፋጣኝ ሰላማዊ መፍትሔዎችን መውሰድ ያስፈልጋል" ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጠየቀ።

ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ የተባለው የሲቪክ ድርጅት ደግሞ ችግሩ "በሥልጣን ሽኩቻ" ምክንያት መፈጠሩን ገልፆ፤ ይህንን ተከትሎ "በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየታዩ ነው" ብሏል።

"ትግራይ ውስጥ የጦርነት ደመና እያንዣበበ ነው" ያሉት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ የፌዴራሉ መንግሥት ሕግን መሠረት አድርጎ ለችግሩ መፍትሔ እንዲያበጅ ሲሉ ጠይቀዋል።

አለመግባባቱ "የሰፈነውን አንጻራዊ ሰላምና መረጋጋት ወደ ኋላ ሊመልስ የሚችል ነው" - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የትግራይ ክልል ችግሮች እንዲሰክኑ ጥሪ ባደረገበት መግለጫው "የፖለቲካ ልዩነቶች በምክክርና በመግባባት ሕግን መሠረት በማድረግ እንዲፈቱ" ጠይቋል።

ኢሰመኮ "በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ እና ውጪ በሚገኙ እና የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) መሪዎች መሆናቸውን በሚገልጹ አካላት" መካከል ከተከሰተው አለመግባባት ጋር ተያይዞ በክልሉ ለወራት የዘለቀውና "ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አሳሳቢነቱ እየጨመረ የመጣው" ባለው ውጥረት በክልሉ አጠቃላይ ሰላም እና የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያለውን አንድምታ እየተከታተለ መሆኑን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የትግራይ ክልል ችግሮች እንዲሰክኑ ጥሪ ባደረገበት መግለጫው "የፖለቲካ ልዩነቶች በምክክርና በመግባባት ሕግን መሠረት በማድረግ እንዲፈቱ" ጠይቋል።ምስል፦ Million Hailesillassie/DW

ኤርትራ የህወሓትን “የውስጥ የፖለቲካ ሽኩቻ የማባባስ ፍላጎት የላትም” - የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር

ኮሚሽኑ አለመግባባቱ በክልሉ "የሰፈነውን አንጻራዊ ሰላምና መረጋጋት ወደ ኋላ ሊመልስ የሚችል" ነው ብሏል። ሁሉም አካላት ችግሩን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ እንዲሁም "የፖለቲካ ልዩነቶች በምክክርና በመግባባት ሕግን መሠረት በማድረግ እንዲፈቱ" ጥሪውን አድርጓል።"ትግራይ ውስጥ የጦርነት ደመና እያዣበበ ነው" - ትዴፓ

ለዚህ ችግር የሕወሓትን አመራር ተጠያቂ ያደረጉት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ በክልሉ ብርቱ ችግር መደቀኑን ገልፀዋ።

"ትግራይ ውስጥ በአጭሩ የጦርነት ደመና እያንዣበበ ነው ያለው"የሕወሓት መሥራች ከነበሩት አንዱ የሆኑትና ሌላ ፓርቲ አቋቁመው ድርጅቱን የሚታገሉት ዶክተር አረጋዊ በርሄ የሕወሓት መከፋፈል የክልሉን ፖለቲካዊ ችግር ማወሰሰቡን  ገልፀዋል።

"የሕወሓት አመራር በቅርብ ጊዜ - ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ ለሦስት ተከፍሎ እርስ በርሱ ለሥልጣን ሽሚያ ሲወዳደር የሕዝቡን ችግር ቁጥር ውስጥ አላስገባውም"

በትግራይ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ

የክልሉ ችግር የሥልጣን ሽኩቻ ያመጣው ሊባል ይችላል - የሲቪክ ድርጅት

ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ የተባለ ሲቪክ ድርጅት "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የታጠቁ ኃይሎች በኃይል ወደተለያዩ የክልሉ አስተዳደር ጽ/ቤቶች በመግባታቸው ምክንያት በአንድ አንድ ቦታዎች ላይ አለመረጋጋት የተፈጠረ መሆኑን መረዳት ችለናል" ብሏል፡፡ 

በመላው የትግራይ ክልል አከባቢዎች "ሰዎችን በኃይል አፍኖ የማሰር እና የማስፈራራት እንቅስቃሴዎች እንዳሉ መረጃ ዶርሶናል" ሲልም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። 

የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መብርሂ ብርሃነ ችግሩን ከሥልጣን ሽሚያ ጋር አያይዘውታል።"የስልጣን ሽኩቻ ልንለው እንችላለን። በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ አካባቢዎች ከባድ የሆኑ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየታዩ ይገኛሉ"

አቶ ጌታቸው ረዳ አዲስ አበባ ላይ የሰጡት መግለጫ

የሕወሓት አንድ አንጃ እና የውጭ ኃይል ግንኙነት

ኤርትራ የህወሓትን “የውስጥ የፖለቲካ ሽኩቻ የማባባስ ፍላጎት እንደሌላት" በቅርቡ አስታውቃላች። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ግን የተወሰኑ ወታደራዊ እና የፖለቲካ አመራሮች ከኤርትራ ጋር ግንኙነት እንዳላቸው አዲስ አበበ ላይ አስቀድመው በሰጡት መግለጫ ጠቅሰው ነበር። 

ይህንንም የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌድዮን ጢሞትዮስም አርብ ዕለት አዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኙ ዲፕሎማቶች ማብራሪያ ሲሰጡ ደግመውታል። 

ምንም እንኳን በዶክተር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራው የሕወሓት ቡድን "ከኤርትራ መንግሥት ጋር የሚደረግ ግንኙነት የለም” ሲል ያስታወቀ ቢሆንም። 

የትግራይ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በሦስት ጀነራሎች ላይ የተላለፈውን እግድ ተቃወመ

ዶክተር አረጋዊ በርሄ ይሄኛው የሕወሓት ቡድን ከኤርትራ ጋር ግንኙነት እንደሚያደርግ እናውቃለን ብለዋል።

"የሕወሓት አመራር እየጋበዘ በአካባቢ ያሉ ኃይሎች አብረውት በፌዴራል መንግሥት ላይ ተጽዕኖ እንዲፈጠር እያደረጉ ናቸው" "ተጠያቂነት ሊኖር ይገባል" ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች እንቅስቃሴው "እጅግ አሳሳቢ ነው" ያሉት የቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ የሥራ ኃላፊ የዜጎች መብቶች ከለላ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።

"የሲቪል ሰዎች ደህንነት - የአከል ደህንነት፣ የሕይወት ደህንነት እነዚህ በሙሉ ሁሌ መጠበቅ ያለባቸው መብቶች ናቸው።" በዚህ ሁሉ የክልሉ ወቅታዊ ኹኔታ አስተያየት የሰጡ ልዩ ልዩ አካላት በአንድ ነገር ተመሳሳይ አቋም አራምደዋል። ይህም የፕሪቶሪያው ዘላቂ የግጭት ማቆም ስምምነት ይተግበር የሚለው ነው።

ሰለሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW