ለአማራ ክልል እርዳታ ፈላጊዎች 102 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተባለ
ዓርብ፣ የካቲት 21 2017
ለአማራ ክልል እርዳታ ፈላጊዎች 102 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተባለ
በአማራ ክልል በፈረንጆቹ 2025 አጠቃላይ 102 ቢሊዮን ብር ለሰብአዊና ማህበራዊ አገልግሎት የሚውል ገንዝብ እንደሚያስፈልግ የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፣ በአማራ ክልል ከ2.7 ሚሊዮን በላይ እርዳታ ፈላጊ ህዝብ መኖሩም ታውቋል፡፡
በአማራ ክልል ያለውን ማህበራዊ ቀውስ ለማገዝ እገዛ ያስፈልጋል
ቀደም ሲል በኮቪድ 19ና በሰሜኑ ጦርነት፣ አሁን ደግሞ በክልሉ ባለው የሠላም እጦት ምክንያት በአማራ ክልል ሰብአዊ ቀውሱ በከፋ ሁኔታ መባባሱ ይታወቃል፡፡ የሰብአዊ እርዳታ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ምክክር የአማራ ክልል የሥራ ኃላፊዎች ትናንት በአዲስ አበባ ከዓለማቀፍ የእርዳታ ሲጪና የልማት ድርጅት ተወካዮች፣ እንዲሁም ከአንዳንድ አገራት አባሳደሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ እንደተገለፀው፣ በክልሉ ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ 6ሺህ154 ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ማህበራዊ ተቋማት መውደማቸው ተመልክቷል፡፡ ከ4 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችም በተከሰቱ ጦርነቶች ምክንያት ከትምህርት ውጪ መሆናቸው በተለያዩ ጊዜዎች ተግልጧል።የቱርክ ካምፕ የአማራ ክልል ተፈናቃዮች የድረሱልን ጥሪ
በአማራ ክልል 2.7 ሚሊዮን እርዳታ ጠባቂዎች አሉ
የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዳይሬክተር አቶ ብርሀኑ ዘውዱ በሰጡን ተጨማሪ ማብራሪያ በክልሉ 2. 7 ሚሊዮን እርዳታ ፋሊጊ ማህበረሰብ እንደሚግኝና በፈረንጆቹ 2025 ለነዚህ የማህበረስብ ክፍሎች ለዕለት እርዳታና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች የሚል 102 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ብለዋል።
አሁን ከተፈጠረው ከአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት ድጋፍ ጋር ተያይዞ በተለይ በ4 ዞኖች ችግሩ መባባሱን ነው ዳይሬክተሩ ያመለከቱት፡፡የአማራ ክልል ተፈናቃዮች አቤቱታ
ችግሩ በ4 ዞኖች የበረታ ነው
የምግብ እህል አቅርቦትን ጨምሮ የአሜሪካ የተራዶዕ ድርጅት (USAID) በቋሚነት ሲያግዝ እንደነበር አመልክተዋል፣ በተለይ ዋግኽምራ፣ ሰሜን ጎንደር፣ ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ወሎ አካባቢዎች በዚህ ድርጅት ይታገዙ እንደነበር ነው ያስታወሱት፡፡ በነዚህ ዞኖች አሁን ከድርጅቱ ድጋፍ መቋረት ጋር ተያይዞ ችግር ውስጥ የገቡ እንደሆነ አስረድተዋል። የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው በዚሁ ይምክክር መድርክ ላይ የተለያዩ ዓለማቅፍ ደርጅት ተወካዮችና ሌሎች አካላት መገነታቸውንም አቶ ብርሀኑ ተናግረዋል፡፡ “ አምባሳደሮች፣ የተባበሩት መንግሥታት ተወካዮች፣ የዓለማቀፍ ረጂ ድርጅት ተወካይ ኃላፊዎች” ነበሩ ነው ያሉት፡፡ እንኚህ አካላት ከውይይቱ ያገኙትን ግብዓት ወስደው ከተመለከቱት በኋላ በግንኙንት አግባባችን መሠረት ምላሸንደሚገኝ ገልጠዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ ባለፉት 4 ዓመታት ክልሉ በኮቪድ፣ በአየር ለውጥና በጦርነት ምክንያት ለበርካታ ሰብአዊ ፣ ስነልቦናዊ፣ማህበራዊና እኮኖሚያዊ ቀውሶች መዳረጉን ጠቅሰው ዓለማቀፉ ማህበረሰብ ለክልሉ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የተገኙ የአንዳንድ ዓለማቀፍ ተቋማት ተወካዮች ጉዳዩን በትኩርት እንደሚመለከቱ መግለፃቸውንም አቶ ብርሀኑ አመልክተዋል።
ዓለምነው መኮንን
አዜብ ታደሰ
ዮሃንስ ገብረግዚአብሔር