1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አንዳርጋቸው ጽጌ ከእስር ተለቀቁ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 21 2010

ወደ አራት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ የቆዩት የተቃዋሚው የግንቦት ሰባት የነጻነት የዴሞክራሲ እና የፍትህ  ንቅናቄ ዋና ጸሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ዛሬ ማምሻውን ከእስር ተፈተዋል። ቤተሰቦቻቸው ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ደጋፊዎቻቸው ዛሬ አቶ አንዳርጋቸው አዲስ አበባ የሚገኘው የአባታቸው ቤት ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Karte Äthiopien englisch

ለአቶ አንዳርጋቸው የተደረገ አቀባበል

This browser does not support the audio element.

ወደ አራት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በእስር ላይ የቆዩት የተቃዋሚው የግንቦት ሰባት የነጻነት የዴሞክራሲ እና የፍትህ  ንቅናቄ ዋና ጸሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ዛሬ ማምሻውን ከእስር ተፈተዋል። ቤተሰቦቻቸው ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ደጋፊዎቻቸው ዛሬ አቶ አንዳርጋቸው አዲስ አበባ የሚገኘው የአባታቸው ቤት ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የአቶ አንዳርጋቸው አቀባበል ኮሚቴ አስተባባሪ ፖለቲከኛ ዳንኤል ሺበሺ እንደተናገሩት በስፍራው በርካታ ህዝብ ተገኝቶ ነው የተቀበላቸው። አቶ ዳንኤል አቶ አንዳርጋቸው አዲስ አበባ እንደሚቆዩም ነግረውኛል ብለዋል። ከአቶ ዳንኤል ሺበሺ ጋር የተደረገው ቃለ ምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ማዳመጥ ይቻላል።

ኂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW