1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ
ኤኮኖሚሰሜን አሜሪካ

ለአዲሱ የዶናልድ ትራምፕ ቀረጥ የአውሮጳ ህብረት ምላሽ ምን ይሆን ?

ሐሙስ፣ መጋቢት 25 2017

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሃገራት ላይ የጣሉት አዲስ ቀረጥ ዓለምን አስደንግጧል። አስር በመቶ ቀረጥ ዝቅተኛ ሆኖ በተቆረጠበት በአዲሱ ቀረጥ የአሜሪካ ወዳጅ ሃገራት አልቀረላቸውም ። በአዲሱ ቀረጥ ውስጥ የአሜሪካ የቅርብ አጋር እና ወዳጅ የሆነው የአውሮጳ ህብረት የ20 ከመቶ ታሪፍ ተጥሎበታል።

Symbolbild Handelskrieg USA und EU
ምስል፦ Imago/Ralph Peters

የአውሮጳ ህብረት ለዶናልድ ትራምፕ ቀረጥ ምን ይመልስ ይሆን?

This browser does not support the audio element.

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሃገራት ላይ የጣሉት አዲስ ቀረጥ ዓለምን አስደንግጧል። አስር በመቶ ቀረጥ ዝቅተኛ ሆኖ በተቆረጠበት በአዲሱ ቀረጥ የአሜሪካ ወዳጅ ሃገራት አልቀረላቸውም ። በአዲሱ ቀረጥ ውስጥ የአሜሪካ የቅርብ አጋር እና ወዳጅ የሆነው የአውሮጳ ህብረት የ20 ከመቶ ታሪፍ ተጥሎበታል።

 

ቀደም ሲል በብረታ ብረት እና በአልሙኒየም ምርቶች ላይ ተመሳሳይ ቀረጥ ተጥሎበት የነበረው ክፍለ ዓለም አሁን ለትራምፕ ርምጃ አጸፋውን ይመለስ ይሆን እየተጠበቀ ነው።

 

 

የአውሮጳ ኅብረት የአጸፋ ርምጃ በአሜሪካን የታሪፍ ጭማሪ ላይ

ህብረቱ የቀድሞ ወዳጅነቱን ላለማጣት ነገሮችን በትዕግስት ከመጠበቅ እና የሚመጣበትን ዓለማቀፍ ተጽዕኖ ለማመጣጠን የሚወስደው እርምጃ ተጠባቂ ነው። ይህንኑ ተከትሎ ብራሰልስ የሚገኙት  የህብረቱ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ እየመከሩ ሲሆን በአሜሪካ ላይ ከሚወስዱት የአጸፋ ርምጃ በተጨማሪ የንግዱን ጦርነት የሚቋቋሙበት አዲስ የገበያ መዳረሻ ማሰሳቸው እንደማይቀር እየተነገረ ነው።

ቀደም ሲል በብረታ ብረት እና በአልሙኒየም ምርቶች ላይ ተመሳሳይ ቀረጥ ተጥሎበት የነበረው ክፍለ ዓለም አሁን ለትራምፕ ርምጃ አጸፋውን ይመለስ ይሆን እየተጠበቀ ነው።ምስል፦ Daniel Kalker/picture alliance

የአውሮጳ ህብረት መሪዎች ፓሪስ ውስጥ ሊገናኙ ነው

ትንናሽ የኤኮኖሚ አቅም ያላቸውን እና በማደግ ላይ ያሉ ሃገራትን ጨምሮ ባዳረሰው አዲሱ የትራምፕ ቀረጥ ዐለም አዲስ የንግድ ጦርነት ውስጥ መግባቷ ርግጥ ስለመሆኑ ተንታኞች እየገለጹ ነው ። የአውሮጳ ህብረት በተናጥል የሚወስደው የአጸፋ ርምጃ በርግጥ ምን ይሆን ? 

ገበያው ንጉሴ 

ታምራት ዲንሳ 

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW