1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለአፍሪቃ ገበያ የተሰራው ርካሽ ስልክ

Eshete Bekeleረቡዕ፣ ነሐሴ 20 2007

ጉግል ኩባንያ በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ ላቀርበው ነው ያለውን አንድሮይድ አንድ የተሰኘ ዘመናዊ ስልክ ስራ እያጠናቀቀ ነው። የስልኩን አገልግሎት የሚያቀላጥፈው ፕሮግራም(ኦፕሬቲንግ ሲስተም) ከአንድ አመት በፊት በእስያ ገበያ ቀርቦ ስኬታማ ሆኖ ነበር።

Twitter Screenshot Infinix Hot 2
ምስል twitter.com

[No title]

This browser does not support the audio element.

ለድሃ የኢንተርኔት ፈላጊዎች በጎግል ኩባንያ የተዘጋጀው አንድሮይድ አንድ (Android One) ከአፍሪቃ ደርሷል። ይህ ማለት በአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም የሚሰራውን ዘመናዊ ስልክ በ87 ዶላር ወይም 1,784.77አካባቢ ብር መሸመት ይቻላል ማለት ነው። በናይጄሪያ የእጅ ስልኮችንና መሰል ቁሳቁሶችን በሚመዝነውና ደረጃ በሚያወጣው ሞቢሊቲ አሬና የተሰኘ የኢንተርኔት አምደ መረብ ሃላፊ የሆኑት ግላዲስ ንዋቹኩ «በጣም ጥሩ ነው። እጅግ ውድና ቅንጡ አይደለም። በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረበ ስልክ ነው። በዚህ ተመን በጣም ጥሩ ነው።»ሲሉ ስለ አዲሱ የጎግል ስልክ ይናገራሉ።

ምስል picture-alliance/dpa

ስልኩ ለአፍሪቃ የቀረበው መሰል ርካሽ ስልኮች በብዛት ለገበያ በሚቀርቡበት በእስያ በኩል ነው። ስልኮቹ ዘገምተኛ የኢንተርኔት አገልግሎት ባሉባቸው አካባቢዎችና የኃይል መቆራረጥ ሲከሰት ድጋፍ የሚያደርጉ መልኮች አሉት። ስልኩ ረጅም የባትሪ እድሜ፤ ሁለት የሲም ካርድ ማስገቢያና የኤፍ.ኤም. ሬዲዮ መፈለጊያ ተበጅቶለታል ተብሏል። ዩ. ቲዩብ ከተሰኘው የኢንተርኔት አገልግሎት የቪዲዮ ምስሎችን እስከ 48 ሰዓት ማከማቸትና የኢንተርኔት አገልግሎቱ ዘገምተኛ በሆነበት ወቅትም መከታተል የሚያስችል ነው። ሩሻብ ዶሺ ካናሊስ በተሰኘ የምርምር ተቋም ተንታኝ ናቸው።

« ስልኩ የተሰራው ጉግል ለአከፋፋዮች ባቀረበው መርህ መሰረት ነው። ስለዚህ ተገልጋዮች ፍላጎታቸውን የሚያሟላ ጥራት ያለው ስልክ ይኖራቸዋል። በሌሎች አከፋፋዮች እንደሚደረገው ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት ብዛት ያላቸው አፕልኬሽኖች አይጫንባቸውም።»

አሁን በአፍሪቃ ገበያ የቀረበው አንድሮይድ አንድ ሆት ሁለት (HOT-2)የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። ስልኩ የሚመረተው የሆንግ ኮንግበሚገኘዉ ኢንፊኒክስ በተሰኘው ኩባንያ ነው። አሁን በናይጄሪያ ሱቆችና የድረ-ገጽ ማሻሻጫዎች ለገበያ ቀርቧል። ኬንያና አይቮሪኮስትን ጨምሮ በአምስት የአፍሪቃ አገሮች ለገበያ እንደሚቀርብ ጉግል አስታውቋል። እንደገና ግላዲስ ንዋቹኩ

«ስልኩ በአንድሮይድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሎሊፖፕ የተሰኘው አዲስ ፕሮግራም የተሰራ ነው። በዚህ ተመን እንዲህ አይነት አገልግሎት ማቅረብ የተለመደ አይደለም። በተለይ እዚህ ናይጄሪያ። አሁን በገበያ ላይ ያሉት እጅግ ዘመናዊ ሲሆኑ እንዲህ አይነት አገልግሎት ለማግኘት ከፍተኛ ገንዘብ ያስከፍላሉ።»

ቴክኖሎጂውን የሚከታተሉ ተንታኞች በአፍሪቃ የስልክ ኢንተርኔት አጠቃቀም በጎርጎሮሳዊው 2019 ዓ.ም. በ2000 በመቶ እድገት ያሳያል ሲሉ ተንብየዋል። ይህ አንድሮይድን ለአምስት ቢሊዮን ሰዎች ለማቅረብ ላቀደው ጉግል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል። ኩባንያው ምርቱን የሚያቀርብባቸው ስድስት አገሮች ወደ 380 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ አላቸው። አርተር ጎልድስሚዝ ዎርልድ ዋይድ ዎርክስ (World Wide Worx) በተሰኘ የደቡብ አፍሪቃ የቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ተቋም ሃላፊ ናቸው።

ምስል dapd

«ሌሎቹ የዓለም ክፍሎች ከፍተኛ የኢንተርኔት ግልጋሎት አላቸው። እናም በብዙዎቹ ክፍሎች ገበያው በብዙ መንገዶች ተዳክሟል። በአፍሪቃ ግን ከፍተኛ የማደግ አቅም አለ። እንደ ጉግልና ማይክሮሶፍት ያሉ ኩባንያዎች ደግሞ የዚህ እድገት አካል መሆን ይሻሉ።»

የአፍሪቃ ዘመናዊ የስልክ ገበያ በአህጉሪቱና የቻይና ምርቶች ቢጥለቀለቅም ጉግል እና አንድሮይድ አንድ ስልኮች ቀስ በቀስ ወደገበያዉ እየገቡ ይሄዳሉ ተብሎ ይታሰባል።

አሽቶሽ ፓንዴ/እሸቴ በቀለ

ሸዋዬ ለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW