ለዩክሬን ዳግም ግንባታ መዋጮ
ሐሙስ፣ ሰኔ 15 2015![Ukraine Rave-Aufräumarbeiten in Yahidne, Chernihiv](https://static.dw.com/image/66005400_800.webp)
ማስታወቂያ
የዩክሬንን መንግስት የሚያስታጥቁት ምዕራባዉያን መንግስታት በጦርነት የወደመዉን የዩክሬንን የመሠረተ ልማት አዉታር መልሶ ለመገንባት ወደ 7 ቢሊዮን ዶላር እያዋጡ ነዉ።ለንደን-ብሪታንያ በተሰየመዉ የገንዘብ መዋጮ ጉባኤ ላይ ከፍተኛዉን ገንዘብ ለመስጠት ቃል የገቡት ዩናይትድ ስቴትስ የአዉሮጳ ሕብረትና ብሪታንያ ናቸዉ።ዩክሬንና ሩሲያ የገጠሙት ጦርነት በተፋፋመበት በዚሕ ወቅት ለዳግም ግንባታ ገንዘብ መዋጣቱ አንዳድ ታዛቢዎችን ግራ ማጋባቱ አልቀረም።ሥለገንዘብ መዋጮዉ የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ