የደቡብ ሱዳን የፖለቲካ ቀውስ
ሐሙስ፣ ግንቦት 23 2010
ማስታወቂያ
ዩናይትድ ስቴትስ በ6 የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ባቀረበችው ሀሳብ ላይ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ዛሬ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። ማዕቀቡም የጉዞ እና የገንዘብ ዝውውር እገዳን ያካትታል። አሜሪካን ማዕቀብ ይጣልባቸው ካለቻቸው ባለሥልጣናት መካከል የመከላከያ እና የማስታወቂያ ሚኒስትሮች እንዲሁም የቀድሞ የጦር ኃይል አዛዥ ይገኙበታል።የናይሮቢው ወኪላችን ቻላቸው ታደሰ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ቻላቸው ታደሰ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ