1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ለደቡብ አፍሪቃ የጎርፍ ተጎጂዎች የኢትዮጵያና የኤርትራዉያን ድጋፍ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 17 2014

በደቡብ አፍሪቃዋ ከተማ ደርባን እና አካባቢዋ በቅርቡ ተከስቶ በነበረው የጎርፍ አደጋ ከ400 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ከ 40 ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ ቤት አልባ ሆነዋል።በርካታ ሰዎችም አሁን ድረስ የደረሱበት አይታወቅም። በአሁኑ ሰዓት ፍለጋው እና የመልሶ ማቋቋሙ ቢቀጥልም በተጎዱት አካባቢዎች ከፍተኛ የመጠጥ ውኃ ችግር እንዳለ ተዘግቧል።  

Südafrika Durban | Hilfe aus Äthiopien und Eritrea nach Überflutung
ምስል፦ Cosmos Michael

ለደቡብ አፍሪቃ የጎርፍ ተጎጂዎች የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ቢዝነስ ኮሙኒቲ የሚያደርገው ድጋፍ

This browser does not support the audio element.

በደቡብ አፍሪቃዋ ከተማ ደርባን እና አካባቢዋ በቅርቡ ተከስቶ በነበረው የጎርፍ አደጋ ከ400 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ከ 40 ሺ በላይ ሰዎች ደግሞ ቤት አልባ ሆነዋል።በርካታ ሰዎችም አሁን ድረስ የደረሱበት አይታወቅም። በአሁኑ ሰዓት ፍለጋው እና የመልሶ ማቋቋሙ ቢቀጥልም በተጎዱት አካባቢዎች ከፍተኛ የመጠጥ ውኃ ችግር እንዳለ ተዘግቧል።  አቶ ኮስሞስ ገብረ ሚካኤል የተባሉ የደርባን ከተማ ነዋሪ ለዶይደ ቬለ እንደገለፁት በዚህ ከፍተኛ ጉዳት በደረሰበት አካባቢ በርካታ ኢትዮጵያውያን ይኖራሉ ወይም ይሰሩ ነበር። አቶ ኮስሞስ መደበኛ ስራቸው ፍርድ ቤት ውስጥ ሲሆን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ቢዝነስ ኮሙኒቲም አባል ናቸው። እሳቸው እንደሚሉት« ከደቡብ አፍሪቃ ማህበረሰቡ ጋር ያለው ቁርኝት ላይ » እስካሁን ብዙም አልተሰራበትም ነበር። ስለሆነም አሁን ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመው የገፅታ ግንባታ ለማድረግ በጎርፍ ለተጎዱ ሰዎች ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ርዳታ እያሰባሰቡ ይገኛሉ።

ልደት አበበ

አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW