1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ለደን ጥበቃ የኅብረተሰብ ተሳትፎ

ማክሰኞ፣ ጥር 7 2005

የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰ መሄዱ ተደጋግሞ የተገለፀ ጉዳይ ነዉ። በአንዳንድ አካባቢዎች ጭርሱን ተራቆቶ የነበረዉ ስፍራ በተለያዩ ስልቶች እንዲያገግም መደረጉ ቢነገርም ይህ ደን የሚባለዉንና የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት አይተካም የሚሉ ወገኖች አሉ።

ምስል፦ JENNY VAUGHAN/AFP/GettyImages

በሀገሪቱ የተሻለ የደን ሃብት ይገኝባቸዋል የሚባሉ አካባቢዎች ሁኔታም ከወን ወደቀን ለጉዳት መዳረጋቸዉ ቢገለፅም ኅብረተሰቡን በማሳተፍ ዉጤት ለማምጣት ጥረት ተጀምሯል።

አቶ ሉሉ ሊካሳ በፋርም አፍሪካና SOS ሳህል ፕሮጀክት የባሌ ፕሮግራም አስተባባሪ ናቸዉ። ለረዥም ዓመታት ጠባቂዎች እየተቀጠሩ ይከታተሉት የነበረዉ የደን ሃብት ከጭፍጨፋ ባለመዳኑ አዲስ ስልት ማለትም አሳታፊ የደን አስተዳደር መርሃግብር ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን ነዉ የገለፁልን።

ምስል፦ DW

የደን ሃብትን መጠበቅ ለአካባቢዉ ኗሪዎች ከሚሰጠዉ የዕለት ከዕለት ጥቅም ባሻገር የአየር ንብረት ሚዛንን በመጠበቅ ደኑ ዉስጥ የሚገኘዉን ብዝሃ ህይወት እንደሚታደግ ይታመናል። የደን ሃብት ጥበቃ በአንድ ተቋም ወይም መንግስታዊ መስሪያ ቤት ብቻ የሚከናወን ከሆነ የተፈለገዉን ዉጤት ማምጣት እንደማያስችል ከታየበት ተሞክሮ በመነሳት ላለፉት ዓመታት ኅብረተሰቡን ያሳተፈ የደን አስተዳደር ሥራ ላይ ዉሏል።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW