ለጤና ሚኒስቴር የተደረገው የቁሳቁስ ድጋፍ
ሐሙስ፣ መጋቢት 30 2013
ማስታወቂያ
በምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት (IGAD) እና በአውሮጳ ሕብረት ኢትዮጵያ የኮሮና ተኅዋሲ ወረርሽኝን ለመግታት የምታደርገውን ጥረት የሚያግዝ የ60 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ። የተቋማቱ ባለሥልጣናት ዛሬ በአዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር ድጋፉን ሲያስረክቡ ወረርሽኙ ሊያድርስ የሚችለውን ቀውስ ለመቋቋም መሰል ድጋፎችን ማድረግ እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል፡፡
የኮሮና ተዋሲ ወረርሽኝ በሌሎች የጤና እክሎች ተደራሽነት ላይ የጎላ ተፅእኖን አሳርፏል ያሉት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጃ ዱጉማ ድጋፉ መሰል ጫናዎችን ለመቋቋም ይረዳል ብለዋል።
ስዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ
ኂሩት መለሰ