1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለፖለቲካ እስረኞች የሚጠየቀው ፍትህ

እሑድ፣ ታኅሣሥ 29 2010

ኢትዮጵያ ውስጥ ላለፉት 26 ዓመታት ከፖለቲካ እና ሃሳብን በነጻነት ከመግለፅ ጋር በተገናኘ በርካታ ዜጎች መታሰራቸዉን በየጊዜ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋማት እና የሀገሪቱ የተቃውሞ ፖለቲካ ፓርቲዎች ያሳስባሉ። መንግሥት ያሰራቸዉን እንደፈታይ ይጠይቃሉ።

Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

ውይይት፦ ለፖለቲካ እስረኞች የሚጠየቀው ፍትህ

This browser does not support the audio element.

 በሀገር ውስጥ ከህዝቡ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች የመጡበት የሀገሪቱ መንግሥት ከተቃዋሚዎቹ ጋር ለመደራደር በወሰነበት ጊዜ ከፓርቲዎቹ ከቀረቡ ጥያቄዎች አንዱ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ የሚለው ነዉ። ይኸው አቤቱታ በበይነ መረብ ሳይቀር የታሰሩትን ሰዎች ስም፣ የታሰሩበትን ምክንያት እና በእስር ላይ የደረሰባቸው በመዘርዘር ትኩረት ለመሳብ ተሞክሯል።የፖለቲካ እስተኞች በሀገሪቱ የሉም የሚለዉ  መንግሥት፤ ከሰሞኑ በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው እና ሌሎች ግለሰቦች ያላቸዉን ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት እንደሚፈታ ጠቁሟል። ዶቼ ቬለ በበይነ መረብ « ፍትህ ለሕሊና እስረኞች» በሚል ዘመቻ ካካሄዱት መካከል ከተወሰኑት ጋር ለፖለቲካ እስረኞች የሚጠየቀው ፍትህ እና መንግሥት የሰጠውን ፍንጭ በተመለከተ ውይይት አካሂዷል። ሙሉ ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤ 

ሸዋዬ ለገሠ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW