1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለ18 ሺህ ኢትዮጵያዉያን የዓይን ሞራ ቀዶ ጥገና ተደረገ

ሰኞ፣ ጳጉሜን 4 2011

«ዳይሬክት ኤይድ ኢትዮጵያ» የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በደሴና ወልድያ ሆስፒታሎች ከ 1 ሺህ 700  በላይ ታካሚዎች የዓይን ቀዶ ጥገና ህክምና ሰጠ። በተለያዩ ምክንያቶች የዓይን ብርሃናቸውን ያጡ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር ጥቂት አይደለም። ችግሩን በህክምና ለማስተካከል መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። 

Äthiopien Felege Hiwot-Krankenhaus Katarakt-OP
ምስል DW/A. Mekonnen

በደሴና ወልዲያ ከ1 ሺህ 700 በላይ ወገኖች የዓይን ብርሃናቸውን አግኝተዋል

This browser does not support the audio element.

«ዳይሬክት ኤይድ ኢትዮጵያ» የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በደሴና ወልድያ ሆስፒታሎች ከ 1 ሺህ 700  በላይ ታካሚዎች የዓይን ቀዶ ጥገና ህክምና አደረገ። በተለያዩ ምክንያቶች የዓይን ብርሃናቸውን ያጡ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ቁጥር ጥቂት አይደለም። ችግሩን በህክምና ለማስተካከል መንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። 
ከነዚህ መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች መካከል በኩዬት ባለሀብቶች የተቋቋመው  «ዳሬክት ኤይድ ኢትዮጵያ» አንዱ ነው። ይህ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ሰሞኑን በደሴና ወልዲያ ሆስፒታሎች ባደረገው የዓይን ሞራ ቀዶ ህክምና ከ1 ሺህ 700 በላይ ወገኖች የዓይን ብርሃናቸውን ማግኘታቸውን የዳይሬክት ኤይድ ኢትዮጵያ የዓይን ሞራ ቀዶ ህክምና ዘመቻ አስተባባሪ ዶክተር ጌትነት ንጉሴ ለዶይቼ ቬለ «DW» በስልክ ተናግረዋል።
የደሴ ሆስፒታል ሥራ አስኪጅ አቶ ሰኢድ የሱፍ፣ ህክምናው ከደቡብ ወሎ ዞን በተጨማሪ ከኦሮሞ ብሔረስብና ከሰሜን ሽዋ ዞን አዋሳኝ ወረዳዎች  ለመጡ ታማሚዎችም መሰጠቱን ተናግረዋል። ከህክምና ዘመቻው አስተባባሪዎች መካከል አንዱ የሆኑትና የዓይን ቀዶ ህክምና ሀኪም አቶ አብርሀም አረጋዊ በበኩላቸው በወልዲያው ህክምና ከሰሜን ወሎ ዞን ወረዳዎች መካከል ከትግራይና ደቡብ ጎንደር ወረዳዎች የመጡ ታካሚዎች ህክምናውን እንደተሰጣቸው ተናግረዋል። የዓይን ሞራ ከእድሜ መጨመር ጋር ተያይዞ የሚመጣ ዓይን በሞራ የመሸፈን ችግር እንደሆነ የዳይሬክት ኤይድ ኢትዮጵያ የዓይን ሞራ ቀዶ ህክምና ዘመቻ አስተባባሪ ዶክተር ጌትነት ንጉሴ አመልክተው፣ በኢትዮጵያ ለዓየነ ስውርነት ከሚዳርጉ ችግሮች መካከልም የዓይን ሞራ ግማሽ ያህሉን እንደሚሸፍንም አስረድተዋል። በቀጣይ በደብረማርቆስ፣ ደብረብርሀንና በሌላ አንድ ሆስፒታል 3000 ያህል የዓይን ሞራ ታማሚዎችን በተያዘዉ 2019 የፈረንጆች ዓመት ለማከም እቅድ መያዙን የተናገሩት ዶክተር ጌትነት ለህክምናው መሳካት ትብብር ያደረጉ የዞን መምሪያ የጤና ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን አመስግነዋል።


ዓለምነው መኮንን


አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW