1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለ20 ዓመታት እስር ላይ የሚገኙት የኤርትራ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች

ሐሙስ፣ መስከረም 13 2014

«20 ዓመት ብዙ ነዉ። 20 ዓመት እኮ ያልነበረ ሰዉ ተወልዶ አድጎ ራሱን የቻለ ሰዉ የሚሆንበት ጊዜ ነዉ። ረጅም ነዉ ። ስለታሰሩት ጋዜጠኞች ታሪክ ለመናገር እሞክራለሁ። ድምፅ ለመሆን እሞክራለሁ። ምን ነበሩ በምን ምክንያት ታሰሩ። እንዴት ናቸዉ። የሚለዉን ነገር እናገራለሁ።» ይርጋለም ፍስሃ መብራቱ

Deutschland | Presse- und Meinungsfreiheit in Eritrea
ምስል PEN

ከታሰሩ 20 ዓመት የሞላቸዉ ኤርትራዉያን ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች

This browser does not support the audio element.

« 20 ዓመት ብዙ ነዉ። ረጅም ነዉ 20 ዓመት እኮ ያልነበረ ሰዉ፤ ተወልዶ አድጎ ራሱን የቻለ ሰዉ የሚሆንበት ጊዜ ነዉ። ስለታሰሩ ጋዜጠኞች ታሪክ ለመናገር እሞክራለሁ። ድምፅ ለመሆን እሞክራለሁ። ምን ነበሩ በምን ምክንያት ታሰሩ። እንዴት ናቸዉ። የሚለዉን ነገር እናገራለሁ። »

ይርጋለም ፍስሃ መብራቱ ትባላለች። ኤርትራዊት ገጣሚ እና ደራሲ ናት። በኤርትራ ለ 20 ዓመታት እስር ላይ ለሚገኙ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ድምፅ ለመሆን እየታገለችም ነዉ። ገጣሚ ይርጋለም ፍስሃ በኤርትራ «ማይ ሱራ» እስር ቤት ለስድስት ዓመታት ታስራ በ 2015 ዓመተምህረት እንደድል ሆኖ ለመለቀቅ መብቃትዋን ፤ከዝያም በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ከሃገር ለመዉጣት ስትሞክር ዳግም መታሰርዋን ነግራናለች። ከዝያ ነዉ በጎርጎረሳዉያኑ 2018 ዓመት ኤርትራን ለመጨረሻ ጊዜ ለቃ፤ በስደት በተለያየ ሃገራት በኩል ጀርመን ለመግባት የበቃችዉ። ገጣሚ ይርጋለም ጀርመን መኖር ከጀመረች ከሁለት ወራቶች በኋላ ሦስት ዓመት ይሆናታል። ገጣሚ ይርጋለም ባለችበት በጀርመን ኤርትራ ዉስጥ ደብዛቸዉ ለጠፋ ቢያንስ ድምጽ ለመሆን ሰሞኑን እየሰራች ነዉ።  ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ፔን ጀርመን የተባለዉ የፀሐፍያን ማኅበር 20 ዓመታት በእስር ላይ የሚገኙ ከ 21 በላይ ኤርትራዉያን ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ሲል ጥሪ አቅርበዋል። ገጣሚ ይርጋለም ፍስሃ ባለችበት በጀርመን ኤርትራ ዉስጥ በየእስር ቤቱ ደብዛቸዉ ለጠፋ  ቢያንስ ድምፅ ለመሆን እየሰራች ነዉ፤ ከታሰሩት መካከል በከፊል ስማቸዉን እንዲህ ዘርዝራ ለዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ጥሬም እያቀረበች ነዉ።

ምስል PEN/Stefanie Silber

በጀርመን የሚገኘዉ ፔን ጀርመን የተባለዉ የፀሐፍያን ማኅበር ፕሬዚዳንት ሊንደር ሱኮቭ እንደተናገሩት

«በኤርትራ የሚታየዉ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ነዉ።  ስለኤርትራ መፍትሄ ለማምጣት በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጥሮብናል። ኤርትራ በአፍሪቃ የምትገኝ ሰሜን ኮርያ አይነት ሃገር ናት። የፕሬስ ነጻነት የለም ። ብዙ ጋዜጠኞች እና አምደኞች ይሳደዳሉ። አብዛኞቹ ጋዜጠኞችም ቢያንስ ለ 18 ዓመታት እስር ላይ ናቸዉ። በዚህ አይነት ሁኔታ ማንም መኖር አይፈልግም። መኖርም አይቻልም። ስለዚህም ሁኔታዉን ለመቀየር፤ መንግሥትን በመቀየርም፤ ለዉጥ ይመጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን።»   የኤርትራዉ ፕሬዚዳንት አሁን ከኢትዮጵያ ጋር ወዳጅነት መስርተዋል። ምናልባት አሁን ልባቸዉ ይራራ ይሆን? ጋዜጠኞቹ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ ይሆን?

ምስል privat

ሌላዉ ኤርትራዉ ዉስጥ ሰቆቃ ላይ ለሚገኙ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች መለቀቅ ወይም የት እንደሆኑ እንዲነገር የኤርትራ መንግሥትንም ሆነ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በመወትወት ላይ የሚገኘዉ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ሰናይ ገብረመድህን ፤ ከጎርጎረሳዉያኑ 1991 በፊት ኢትዮጵያ ዉስጥ ሳለ በማህቶት፤ ፈርጥ ፤ አብዮታዊ ዲሞክራሲ በሚባሉ ጋዜጣና መጽሔቶች ላይ ይፅፍ ነበር። ኤርትራ ነፃነትዋን እንዳገኘች ኤርትራ አስመራ ዉስጥ በቴሌቭዝን እና በሬድዮ የአማርኛ ክፍል አዘጋጅ ሆኖ ሰርቶአል።  ጋዜጠኛ ሰናይ በአሁኑ ወቅት አዉስትራልያ ነዋሪ ነዉ። ደራሲና ጋዜጠኛ ታሳሪዎቹ የኤርትራ ጋዜጠኞችም ሆኑ ፖለቲከኞች እስር መጀመር ሁኔታ በስፋት አጫዉቶናል።  የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አምስቲ ኢንተርናሽናል ፔን የተባለዉ በጀርመን የሚገኘዉ የጸሐፊዎች ማኅበር በኤርትራ እስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞች እና ፖለቲከኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ሲል ጥሪ አቅርቦአአል። ገጣሚ ይርጋለም መብራቱ ፍስሃ እና ጋዜጠኛ እና ደራሲ ሰናይ ጋዜጠኛ  አንተስ ምን መልክት አለህ ?

 

አዜብ ታደሰ  

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW