1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ዓለም አቀፍ ሽልማት አገኘ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 12 2017

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይስሀቅ ዩሱፍ ለዶይቼ ቬለ ዩኒቨርሲቲው በስምንት ምድቦች በተካሄደው አለም አቀፍ ውድድር በሀረማያ ሀይቅ ላይ የሰራውን ስራ ለውድድር አቅርቦ ማሸነፉን ገልፀዋል

ዩኒቨርስቲዉ ለሽልማት የበቃዉ የነጠፈዉን የሐረማያ ሐይቅ ተመልሶ ዉሐ እንዲያቆር በማስቻሉ ነዉ
የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በእንግሊዝኛ ስያሜው International Green Gown Award  የ2024  አሸናፊ ሆነምስል፦ DW/G. Godae

ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ዓለም አቀፍ ሽልማት አገኘ

This browser does not support the audio element.

የሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እንግሊዝ ሀገር በተካሄደው እና በተለያዩ ዘርፎች ውድድር በሚካሄድበት በእንግሊዝኛ ስያሜው International Green Gown Award  የ2024  አሸናፊ መሆን መቻሉን የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝዳንት ገለፁ።ዩኒቨርሲቲው ከመወዳደሪያ ምድቦቹ ኔቸር ፖዘቲቭ በሚለው ምድብ  በሀረማያ ሀይቅ ላይ ያመጣውን ለውጥ ለውድድሩ ማቅረቡም ተገልጧል ።ከአካባቢው ገፅ ለአመታት ጠፍቶ ዳግም የተመለሰው የሀረማያ ሀይቅ በአሁኑ ሰዓት በተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይስሀቅ ዩሱፍ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

 

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይስሀቅ ዩሱፍ ለዶይቼ ቬለ ዩኒቨርሲቲው በስምንት ምድቦች በተካሄደው አለም አቀፍ ውድድር በሀረማያ ሀይቅ ላይ የሰራውን ስራ ለውድድር አቅርቦ ማሸነፉን ገልፀዋል።ዶ/ር ይስሀቅ ሽልማቱ የተለያዩ ጠቀሜታዎች እንዳሉት አስረድተዋል ።በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሀረማያ ከተማ የሚገኘው የሀረማያ ሀይቅ ለአመታት ከአካባቢው ገፅ ጠፍቶ ዳግም ከተመለሰ በኃላ ስላለበት ይዞታ የተጠየቁት ዶ/ር ይስሀቅ "በጥሩ ሁኔታ" ላይ መሆኑን ገልፀዋል።

በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ይስሀቅ ዩሱፍ ምስል፦ Mesay Teklu/DW

 

አቶ ዳግም የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ ለማህበረሰቡ የተለያየ ጠቀሜታ እያበረከተ ያለው የሀይቁ ውሀ ዳግም እንዳይጠፋ ሌሎች ስራዎች ቢሰሩ መልካም ነው ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።International Green Gown Award ከ2004 ጀምሮ በአለም ደረጃ ዘላቂነት ያለው ለውጥን ለሚያመጡ ዩኒቨርሲቲዎች አንድ የመወዳደርያ መድረክ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

መሳይ ተክሉ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW