«ሕወሓት ከአዲስ አበባ ሌላ ጉዳይ የለውም» ጌታቸው ረዳ
ሰኞ፣ ጥቅምት 29 2014
ማስታወቂያ
በትግራይ ክልል ላይ የተጣሉ ዕቀባዎች ከተነሱ እና የተቋረጡ አገልግሎቶች ከተመለሱ ሕወሓት የተኩስ አቁም ለማድረግ እና ለመደራደር ፍቃደኛ መሆኑን የግንባሩ ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ ። ቃል አቃባዩ ዛሬ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ «ሕወሓት ከአዲስ አበባ ሌላ ጉዳይ የለውም» ብለዋል።
በአፍሪቃ ቀንድ የአፍሪቃ ሕብረት ልዩ ልዑክ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ከሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ጋር ተገናኝተው መነጋገራቸውን ያነሱት አቶ ጌታቸው ፤ የንግግሩ ይዘት በሂደት ያለ በመሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
የሕወሃት ቃል አቃባይ ጌታቸው ረዳ ድርጅታቸዉ ይፈፅማቸዋል ስለተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች፣ ከሕዝብ ስለሚደርስበት ተቃዉሞ፣ ከዩናይትድ ስቴትስ ይሰጠዋል ስለሚባለዉ ድጋፍ፣ ከሌሎች ስምንት ቡድናት ጋር ስለመሰረተዉ ትብብር እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል።
ነጋሽ መሐመድ አነጋግሯቸዋል።