1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህወሓት የጠራው ጠቅላላ ጉባዔ እና በፓርቲ ውስጥ የተፈጠረው ክፍፍል

ሐሙስ፣ ሐምሌ 18 2016

ህወሓት ሊያደርገው ያቀደው ጉባኤ በፓርቲው ቁጥጥር ኮምሽን ተቃውሞ ገጥሞታል። የህወሓት ቁጥጥር ኮምሽን ባወጣው መግለጫ 14ተኛ የህወሓት ጉባኤ ለማድረግ የሚደረገው እንቅስቃሴ በማውገዝ ተወካዮቹ ከጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ራሳቸው ማግለላቸው አስታውቋል።

Äthiopien | Flagge Tigray People’s Liberation Front (TPLF
ምስል Million Haileyessus/DW

ህወሓት «በልዩ ሁኔታ» በፓርቲነት እንዲመዘገብ

This browser does not support the audio element.

ህወሓት ሊያደርገው ያቀደው ጉባኤ በፓርቲው ቁጥጥር ኮምሽን ተቃውሞ ገጥሞታል። የህወሓት ቁጥጥር ኮምሽን ባወጣው መግለጫ 14ተኛ የህወሓት ጉባኤ ለማድረግ የሚደረገው እንቅስቃሴ በማውገዝ ተወካዮቹ ከጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ራሳቸው ማግለላቸው አስታውቋል። ከህወሓት የውስጠ ፓርቲ ውዝግብ በተጨማሪ፥ የሚጠበቀው የህወሓት ሕጋዊ እውቅና የመመለስ ተግባርም ቢሆን አወዛጋቢ ሆኖ፥ ተፈፃሚ ሳይሆን እንደቀጠለ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ሌላ ዙር ጦርነት የሚሸከም ጫንቃ ይኖራታል?

በ50 ዓመት ታሪኩ አጋጥሞት በማያውቅ ከባድ ፈተና ውስጥ መሆኑ የሚገልፀው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፥ በአመራሮቹ መካከል በግልፅ የሚታይ ውዝግብ፣ የአቋም ልዩነት እና ክፍፍል እየተስተዋለ ይገኛል። ባለፈው ሳምንት ካደረገው የከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ በኃላ በሐምሌ ወር ውስጥ ወደ ጉባኤ ለማምራት ስምምነት ላይ ተደርሷል የሚል መግለጫ አውጥቶ የነበረ ቢሆን ትላንት የህወሓት ቁጥጥር ኮምሽን ባሰራጨው መግለጫ ደግሞ 14ተኛ የህወሓት ጉባኤ ለማድረግ የሚደረገው እንቅስቃሴ በማውገዝ የቁጥጥር ኮምሽኑ ተወካዮች ከጉባኤው አዘጋጅ ኮሚቴ ራሳቸው ማግለላቸው አስታውቋል።

የአማራ ክልል መንግሥት «ህወሓት ጦርነት ከፍቶብኛል» አለ

የህወሓት ማእከላዊ ቁጥጥር ኮምሽን እንዳለው የታቀደው የፖርቲው ጉባኤ "የበላይነት አለኝ ባለሀይል" የተጠለፈ በማለት ወቅሶታል። የህወሓት ጉባኤ በአፋጣኝ እንዲደረግ እና እንዲቆይ አልያም እንዲራዘም በሚል በህወሓት አመራሮች እና አባላት መካከል ያለው ልዩነት እንዲሁም የህወሓት ሕጋዊ ሰውነት የመመለስ ጉዳይ ከፓርቲው ተሻግሮ ሌሎችም አቋማቸው እየገለፁ ነው። በሀገሪቱ ካሉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በያዝነው ሳምንት የተወያዩት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አሕመድ፥ ህወሓት ከጉባኤ በፊት ሕጋዊነቱ እንዲያረጋግጥ፥ ይህ ካልሆነ ህወሓት በምርጫ አይሳተፍም እንዲሁም መንግስት መሆን አይችልም፥ ይህም ወደ ጦርነት ይመራል ሲሉ ተናግረዋል።

በ50 ዓመት ታሪኩ አጋጥሞት በማያውቅ ከባድ ፈተና ውስጥ መሆኑ የሚገልፀው ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)፥ በአመራሮቹ መካከል በግልፅ የሚታይ ውዝግብ፣ የአቋም ልዩነት እና ክፍፍል እየተስተዋለ ይገኛል።ምስል Million Haileyessus/DW

ሕወሃት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ ተቃወመ

 ከህወሓት ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ያንፀባረቁት አቋም የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡበት ነው። የሕግ ምሁሩ እና ሂደቱ በቅርበት የሚከታተሉ አቶ ሙስጠፋ ዓብዱ ጉባኤ ማድረግ እና አለማድረግ የአንድ ፓርቲ የውስጥ ጉዳይ እንጂ ወደ ጦርነት ሊመራ የሚችልበት ምንም ዓይነት በቀጥታ የሚገናኝ ምክንያት የለም ይላሉ።

«የህወሓት ከሽብርተኝነት መሰረዝ መልካም ጅምር ነው» የህወሃት ባለሥልጣን

የህወሓት ቁጥጥር ኮምሽን በ14ተኛ የህወሓት ጉባኤ ጉዳይ የሚያንፀባርቀው አቋማ የታቀደው ጉባኤ ግልፅነት የጎደለው እና ምናልባትም ፓርቲ ወደከፋ ክፍፍል ሊመራ የሚችል ነው በሚል ነው። የህወሓት ቁጥጥር ኮምሽን ሊቀመንበር አቶ ተክለብርሃን አርአያ "የጉባኤ ዝግጅቱ፥ አዘጋጅ ኮሚቴው አይደለም እየመራው ያለ ብለን ለማእከላይ ኮሚቴ አስቀድመን ደብዳቤ ፅፈናል። ይሁንና ወደ ማእከላይ ኮሚቴው እንዳይደርስ ታፍኖ ነው የቆየው። በመድረክም ግልፅ አድርገናል። ውስጥ ለውስጥ፣ ፀረ ዴሞክራሲ በሆነ መንገድ ጉባኤ ለማድረግ እየተሞከረ ነው፣ ጉባኤው ከዚህ እንታደገው" ብለዋል።

በትግራይ ክልል ይቋቋማል የተባለው ጊዜያዊ አስተዳደር ጉዳይ

የህወሓት የውስጠ ፓርቲ ውዝግብ እንዳለ ሆኖ በፕሪቶሪያው ውል መሰረት ሊፈፀም የሚጠበቀው የህወሓት ሕጋዊ እውቅና የመመለስ ተግባርም ቢሆን አወዛጋቢ ሆኖ፥ ተፈፃሚ ሳይሆን እየቀጠለ ነው።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ 

እሸቴ በቀለ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW