1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

«ሕዝቡ በስፋት ሳይመክርበት ከእስራኤል ጋር የሚደረግ የግንኙነት ስምምነት አይኖርም»

እሑድ፣ መስከረም 17 2013

ሱዳን ህዝቡ በስፋት ሳይመክርበት ከእስራኤል ጋር የሚደረግ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስምምነት አይኖርም አለች። ሱዳን ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንድትጀምር  በዩናይትድስቴትስ ጫና እየተደረገባት ቢሆንም ሀገሪቱ በሽግግር ላይ መሆኗ ይህን ፍላጎት በፍጥነት ገቢራዊ ማድረግ እንደማይቻል ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ተናግረዋል።

Sudan I Politik I Abdallah Hamdok
ምስል፦ Getty Images/AFP/E. Hamid

ሱዳን ህዝቡ በስፋት ሳይመክርበት ከእስራኤል ጋር የሚደረግ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስምምነት አይኖርም አለች። ሱዳን ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንድትጀምር  በዩናይትድስቴትስ ጫና እየተደረገባት ቢሆንም ሀገሪቱ በሽግግር ላይ መሆኗ ይህን ፍላጎት በፍጥነት ገቢራዊ ማድረግ እንደማይቻል ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሃምዶክ ተናግረዋል። ሃምዶክ ትናንት ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ እንዳሉት «ሱዳን ከዩናይትድስቴትስ የጥቁር መዝገብ ለመውጣት ቀዳሚ ፍላጎቷ ነው። በዚህም ከእስራኤል ጋር ዲፕሎሚሲያዊ ግንኙነት መጀመርን የሚደግፉ ፖለቲከኞች የመኖራቸውን ያህል  አጥብቀው የሚቃወሙ ፖለቲከኞች በርካቶች ናቸው »ብለዋል።« ይህ ደግሞ ሀገራቱ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ውስጥ ውስጡን ጦርነት ውስጥ የማለፋቸው ውጤት ነው »ብለዋል ሃምዶክ። ለዚህ ደግሞ መፍትሄው «ህዝቡ በስፋት መክሮበት የሚበጀውን ውሳኔ ሲያሳልፍ ያኔ ግንኙነቱን ለመጀመር እንችላለን» ሲሉ የሱዳንን ወቅታዊ አቋም አስታውቀዋል። ዩናይትድስቴትስ ልክ  የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች እና ሌሎች እንዳደረጉት ሁሉ ሱዳን ከእስራኤል ጋር እርቅ እንድትፈጽም ብርቱ ፍላጎት እንዳላት የፈረንሳይ ዜና ምንች ዘግቧል ። ሱዳንን ከጥቁር መዝገብ ለመፋቅም የግንኙነቱን መጀመር እንደ ቅድመ ሁኔታ ማስቀመጧ ይነገራል። ሱዳን እጎአ ከ1993 ጀምሮ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ጂሃዲስቶችን ይደግፋሉ በሚል ሱዳን በዩናይትድስቴትስ አሸባሪነትን በመደገፍ የጥቁር መዝገብ ተመዝግባ ቆይታለች።

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW