1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

ሕዝብ እና መንግሥትን በጥርጣሬ ከመተያየት የሚያስወጣ ሥራ እንደሚስፈልግ ተገለፀ

ሰለሞን ሙጬ
ማክሰኞ፣ መስከረም 6 2018

በዚሁ መድረክ ላይ " የኢትዮጵያ የግጭት አዙሪት መንስኤዎች" ምንድን ናቸው በሚለው ላይ አጠር ያለ ገለፃ ያቀረቡት የፖለቲካ ሳይንስ ምኁሩ ዶክተር ሰሚር የሱፍ መንግሥት ስለ ማኅበረሰብ፣ ማኅበረሰብ ደግሞ ስለ መንግሥት ያላቸው አተያይ የተንጋደደ እና እርስ በርስ በጥርጣሬ የተሞላ መሆኑን---

አቶ አሕመድ ሁሴን የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝደንት።ምክር ቤቱ ያዘጋጀዉ የሰላም ጉባኤ ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ተጀምሯል።
አቶ አሕመድ ሁሴን የኢትዮጵያ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝደንት።ምክር ቤቱ ያዘጋጀዉ የሰላም ጉባኤ ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ተጀምሯል።ምስል፦ Solomon Muche/DW

ሕዝብ እና መንግሥትን በጥርጣሬ ከመተያየት የሚያስወጣ ሥራ እንደሚስፈልግ ተገለፀ

This browser does not support the audio element.

ኢትዮጵያ ውስጥ "መንግሥት እና ሕዝብ በከፍተኛ ጥርጣሬ የሚተያዩ ናቸው" ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስ ምኁሩ ዶክተር ሰሚር የሱፍ ተናገሩ።ባለሙያው ይህንን ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ "ጦርነት፣ ግጭት እና ኃይል የታከለበት ውጊያ እንዲቆም" የሚጠይቅ ነው የተባለለት ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ ዛሬ ማግሰኞ በአዲስ አበባ ሲጀመር ነው።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ባዘጋጀው የሰላም ጉባኤ ይህ በሀገሪቱ ቀውስ ያስከተለ ችግር እንዲቀረፍ መንግሥት የሕዝብን ሉዓላዊነት ማክበር፣ ሕዝብም የመንግሥትን ብቸኛ ኃይል የመጠቀም መብት አምኖ መቀበል አለባቸው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት "ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያ" በሚል ዛሬ መስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም ባዘጋጀው ሀገር አቀፍ ጉባኤ "ውይይት እና ምክክር" ከኃይል አማራጭ ይልቅ የችግር መፍቻ አማራጮች እንዲሆኑና ለዚህም "ደፋር እርምጃዎች" እንዲወሰዱ ተጠይቋል።

"ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ መፍታት" የዚህ ዐመት ዐበይት ጉዳይ መሆን እንዳለበት የተናገሩት የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት አቶ አሕመድ ሁሴን "ለሁሉም የግጭት ተፋላሚ ኃይሎች ተግባራዊ የሰላም ጥሪ አድርገዋል።

በዚሁ መድረክ ላይ " የኢትዮጵያ የግጭት አዙሪት መንስኤዎች" ምንድን ናቸው በሚለው ላይ አጠር ያለ ገለፃ ያቀረቡት የፖለቲካ ሳይንስ ምኁሩ ዶክተር ሰሚር የሱፍ መንግሥት ስለ ማኅበረሰብ፣ ማኅበረሰብ ደግሞ ስለ መንግሥት ያላቸው አተያይ የተንጋደደ እና እርስ በርስ በጥርጣሬ የተሞላ መሆኑን አንድ ምክንያት አድርገው በአጽንዖት ጠቅሰዋል።

ይህ ችግር ሥር ነቀል በሆነ መልኩ እንዲፈታ ከተፈለገ እንደ ዶክተር ሰሚር የምርምር ውጤት "መንግሥት የሕዝብን መብት፣ ሉዓላዊነት ተቀብሎ እና አክብሮ መኖር፤ ሕዝብ ደግሞ የመንግሥትን በተለይ የኃይል መሣሪያዎችን በብቸኝነት ተቶጣጥሮ፣ የሕግ የበላይነትን አስከብሮ መሄድን መቀበል" ነው። አንደኛው የሌላኛውን ኃይል እና ሥልጣን መቀበል ከሁሉቱም የግድ ይጠበቃል በማለት ይህ ሲሆን ነው "ሰላማዊ፣ የተረጋጋ እና ዴሞክራሲያዊ ሀገር መፍጠር የምንችለው" ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት አርማ።ምክር ቤቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረጉ ግጭቶች በሚቆሙበት ሥልት ላይ የሚነጋገር የሰላም ጉባኤ አዘጋጅቷል።ምስል፦ Ethiopian Civil society organizations council



የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ሕብረት(ኢሰመድሕ) ዋና ዳይሬክተር አቶ መሱድ ገበየሁ "የተጨበጡ" ያሏቸው ውጤቶች እንዲመጡ ኢትዮጵያ "አዲስ የፖለቲካ ባህል ያስፈልጋታል" ይላሉ። ምክንያት የሚሉት ደግሞ "በማኅበረሰቡ እና በመንግሥት መካከል ያለ አለመግባባት እና አለመተማመን ነው።"

"መንግሥት ሕግ ያስከብር" የሚል ማኅበረሰብ "መንግሥት ሕግ በሚያስከብርበት ጊዜ ደግሞ ሕግ እንዳይከበር የሚንቀሳቀስን ኃይል ሽፋን ይሰጣል" ሲሉም ጠቅሰዋል።ዶክተር ሰሚር ባቀረቡት ጽሑፍ "ተፋላሚ ኃይሎች ከመንግሥት ጋር ለመደራደር ምን አበረታች ጉዳይ አላቸው? መንግሥትም በተመሳሳይ" ለሚለው ሁሉም ምላሽ እንዲሰጥ በሚል ጥያቄው የመፍትሔ አካል እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW