ሕገወጥ ሰዉ አሸጋጋሪዉ መኮብለል
ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2007ማስታወቂያ
ግለሰቡ አቶ ሳሙኤል ቦጋለ የሚባሉ ሲሆን ገንዘቡን ይዘዉ ዱባይ እንደነበሩ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ኒዉዮርክ እንደሚገኙ ተበዳዮች መግለፃቸዉን የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል። በሕገወጥ መንገድ ሰዎችን ከሀገር ሀገር በሚያዘዋዉሩ ላይ መንግሥት ጠበቅ ያለ ርምጃ ለመዉሰድ የሚያስችለዉን እያወጣሁ ነዉ ባለበት በዚህ ወቅት ግለሰቡ በኢንተርፖል ይመጣሉ እየተባለ ጭራሽ ኒዉዮርክ መግባታቸዉን በመስማታቸዉ ቅሬታ እንዳደረባቸዉ ተበደልን የሚሉት ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ