1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኪነ ጥበብ

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 3 ከትዕይንት 1 እስከ 4)

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 14 2010

ወንጀል ተፋላሚዎቹ! አዲስ ተከታታይ ድራማ ጽሑፍ በፌስ ቡክ። በፈጣን የሴራ ፍሰት፥ በአጫጭር ትእይንቶች የተገነባው ድራማ በአይነቱ ለየት ያለ ነው። ይኽ የድራማ ጽሑፍ በዶይቸ ቬለ የአማርኛው ክፍል የፌስቡክ ገፅ የሚቀርብ ሲኾን፤ ለሽልማት የሚያበቃ ነው። ስለ ተሳትፎ እና ውድድሩ ፌስቡክ ገጻችን ላይ በዝርዝር ይገኛል።

09.2015 Crime Fighters MQ amharisch

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 3 ትዕይንት 1)

ሙና የወንድሟ ጳውሎስ ድንገት በሰው እጅ ማለፍ ልቧን አድምቷታል። ባዶ ቤት ውስጥ ዘግታ እየተንሰቀሰቀች ነው። የእጅ ስልኳ ይጠራል።

«ሃይ ሙና! እንዴት ይዞሻል?»

«ምን የምሆን ይመስልሃል ዓለሙ! ያው ወንድሜን እንደሆነ ሉሲ ገድላዋለች።»

«ሙና ስለሱ ገና ምንም አላረጋገጥንም። ወንድምሽን በማጣትሽ በጣም አዝናለሁ። ለቅሶ እና እምባ ግን አይመልሰውም! እመኚኝ ገዳዩን አንጠልጥዬ ለፍርድ እንደማቀርበው ቃል እገባልሽላሁ።»

«ማድረጉ እንደመናገሩ ቀላል ቢሆንማ ምን ነበረበት!»

መርማሪ ዓለሙ እንደቃሉ የወንድሟን ገዳይ ማንንነት ይደርስበት ይኾን?

***  

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 3 ትዕይንት 2)

በሀገሪቱ የዝኆኖች ቁጥር መመናመን የብዙዎች መነጋገሪያ ኾኗል። በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የተወረሱ በርካታ የዝኆን ጥርስ ክምችቶችም ተቃጥለዋል። እሳቱን የለኮሱት የበዓሉ የክብር እንግዳ ዶ/ር ሰናይት ናቸው። የሕገወጥ አዳኞቹ መሪያቸው «ሚስተር ጂ» ከመባሉ ውጪ እነማን እንደሆኑ ፍንጭ አልተገኘም። ዶ/ር ሰናይት ንግግር ሲያሰሙ መርማሪ ከበደ ሙሳ ከተባለ ሰው ጋር ይተዋወቃል። ሙሳ የዝኆን ጥርስ ክምችቶቹ ሲቃጠሉ መመልከቱ በጣም አበሳጭቶታል።

«ምንድን ነው ግን ይህን ያኽል ያበሳጨኽ?»

«ምን መሰለህ፤ እኔ ተፈጥሮን እየተዟዟርኩ ፎቶ አነሳለሁ»   

«እኔ ደግሞ መርማሪ ፖሊስ ነኝ። በጸረ ሕገወጥ አደን ክፍል ውስጥ ነው የምሠራው። ቆይ ግን ደኑ ውስጥ ስትዘዋወር አንድም ጊዜ ሕገወጥ አዳኝ ገጥሞህ አያውቅም?»

«ይቅርታ አንዴ ስልክ ላናግር። ሄሎ ቤቲዬ...እየመጣሁ ነው። ይቅርታ መርማሪ መሄድ አለብኝ።»

መርማሪ ከበደ በበዓል አከባበር ሥነ-ስርዓቱ ላይ የሆነ ፍንጭ ባገኝ ብሎ ዐይኑን ያማትራል። ሙሳ ደግሞ ባዶ ቤት ታቅፋ ወደምትጠብቀው ፍቅረኛው በፍጥነት ገስግሷል።

***  

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 3 ትዕይንት 3)

ከሌሊቱ ለዘጠኝ ሰአት ሩብ ጉዳይ፥ ሙሳ በጭለማ ውስጥ አፍጥጦ ተቀምጧል። ቤቲ ከውጭ በሩን በዝግታ ከፍታ ትገባለች።

«ብራቮ ቤቲ! ልክ ከለሊቱ ለዘኝ ሰዓት እሩብ ጉዳይ ላይ እቤትሽ ከች አልሽ!»

«ውይ ሙሳ! እንዴት ነው ያስደነገጥከኝ! እዚህ ጨለማ ውስጥ ብቻህን ተቀምጠህ ምን ትሠራለህ?»

«ይኸው ደውለሽ በጠራሽኝ መሰረት 3 ሰዓት ሙሉ እዚህ ተጎልቼ ስጠብቅሽ ነበር! ቆይ ግን እኔ ሳልኖር ሳልኖር ቤት የምትገቢው በዚህ ሰዓት ነው ማለት ነው?»

«እረ እኔ አምሽቼ አላውቅም! ዛሬ ጓደኞቼን አግኝቼ ሳላስበው ነው የመሸብኝ።»

«በቃሽ! ማንን ነው ልትሸውጂ የምትፈልጊው? ሁልጊዜም ወደ ቤት የምትመጪው ጠጥተሽና አምሽተሽ ነው።»

«ራስህ በቃህ ሙሳ! ከዚህ በላይ ምንም እንድትናገረኝ አልፈልግም!»

«እንዴ! እና ወዴት ልትሄጂ ነው? ቤቲ…ቤቲ…እባክሽን ብቻዬን ትተሽኝ አትሂጂ!»

***  

ሕገ-ወጥ አዳኞች (ገቢር 3 ትዕይንት 4)

የጳውሎስን ገዳያ ለማግኘት የተጀመረው ምርመራ እንደቀጠለ ነው። ወንጀል መርማሪው ዓለሙ የቴክኒክ ምርመራ ባለሙያዋ ስመኝን ለማነጋገር የምትሠራበት ቤተ-ሙከራ ውስጥ ይገኛል።

«እሺ የጳውሎስ ግድያን በተመለከተ ምን አዲስ ነገር አለ?»

«በሟች ኮምፒውተር ውስጥ አንድ ለሚስተር የተጻፈ የዛቻ ደብዳቤ አግኝተናል።»

«ሚስተር ጂ? ግን እኮ ስለ ሚስተር ማንነት ማንም ሰው አያውቅም!»

«ደብዳቤው ፊርማ ባይኖረውም የተጻፈው ከግድያው በፊት ነው።»

«እና ምን ይላል?»

«ላኪው የቪዲዮ ቅጂ እንዳለው በመግለጽ፤ የሚስተር ጂን ማንነት ለዓለም እንዳላጋልጥ ትንሽ ጉርሻ ቢጤ ያስፈልገኛል የሚል ጽፏል። ቤቴልሄም አራጌ በሚል ስም ወደተመዘገበ ሞባይል ስልክም ተደጋጋሚ መልእክት ልኳል።»

ሟች ጳውሎስ ከሌላ ሴት ጋር ግንኙነት ነበረው የተባለው እውነት ነበር ማለት ነው? መርማሪ ዓለሙ የቤቴልሔም አድራሻ በፍጥነት እንዲገኝ መመሪያ ያስተላልፋል።

***

የድራማውን አራተኛ ክፍል ማለትም ገቢር 4  አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ገቢር 1 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን ቀጣይ ክፍል ማለትም ገቢር  2  አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን አምስተኛ ክፍል ማለትም ገቢር 5 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ገቢር 6 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን የመጀመሪያ ክፍል ማለትም ገቢር 7 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

የድራማውን ቀጣይ ክፍል ማለትም ገቢር 8 አራት ትእይንቶች ይኽን ሲጫኑ ያገኛሉ።

ጀምስ ሙሃንዶ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW