መምህራንን ያስቆጣው የመኖሪያ ቤትና የሃላፊነት አበል ጭማሪ
ዓርብ፣ የካቲት 10 2015ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን የተፈቀደው የመኖሪያ ቤት እና የሀላፊነት አበል በመምህራኖች ዘንድ ቅሬታን አሰነሳ። የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በዚህ ሳምንት ረቡዕ የካቲት 8 ቀን 2015 ዓም በተፃፈ ደብዳቤ የመኖሪያ ቤት እና የሀላፊነት አበል ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈቀደ መሆኑን አስታውቋል ከየካቲት 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን ውሳኔ የተሰጠበት ደብዳቤ ላይ የተገለፀው ጭማሪ እንዳሳዘናቸው አስተያየታቸውን ለዶቼቬለ የሰጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለሙያዎች ተናግረዋል።ዶቼቬለ ስለ ጭማሪውና ቅሬታው የሚመለከታቸውን ሃላፊዎች ለማነጋገር ቢሞክርም አልተሳካም። ሀና ደምሴ ዝርዝሩን አጠናቅራለች።
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪሰ ኮሚሽን እንደጠቀሰው አባሪ በማድረግ ባወጣወ ደብዳብቤ መሰረት በከፈተኛ ትምህርት ተቋማት የመኖሪያ ቤት አበል የተፈቀደው ለፕሬዘዳንት 12 ሺ ለምክትል 10 ሺ ለኮሊጅ ዲኖቸ 3 ሺህ ብር ሲሆን ለምክትል ትምህርት ክፍል ሀላፊዎቸ 1800 ብር ነው ለተቀሩት እንደ የደረጃቸው እና ሀላፊነት ጭማሪ ማድረጉን በደብዳቤ አሳውቋል።
በኢትዮጵያ በየግዜው እየጨመረ ያለው የኑሮ ጫና ለማቅለል እንደዚሁም ለረጅም ግዜ ያልተነካ የደመዎዝ ጭማሪ እንዲሻሻል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ሰናቀርብ ቆይተናል ሲሉ የዪንቨርስቲ መምህር እና የ መምህራንማህበር አባል የሆኑት ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈልጉ መምህር ለዲ ደብሊው ተናግረዋል።
መምህሩ እንደተናገሩት ከወር ደሞዝ ጭማሬ አናሳ መሆንና ሌሎች መፍትሄ ባላገኙ ተደራራቢ ችግሮች መበራከት ምክንያት ሥራ እስከማቆም የሚደርስ አድማ ለማድረግ በምክክር ላይመሆናቸውን ጭምር ለ ዶቼ ቬሊ ተናግረዋል ።
«ደመወዝ እንዲጨመር እሺታን አግኝተን እየጠበቅን ከቆየን በኋላ፣ የቤት ክራይ ዋጋ ጣራ በነካበት ወቅት 1600 ብር መጨመር ፌዝ ነው» ሲሉ ቅሬታቸውን ያስሙት መምሀር እኛ ደብዳቤው በየማህበረ ገፁ ሲታይ ሀሰተኛ መረጃ ነው የመስለን አሁን ካለው የኑሮ ውድነት እና እኛ እንዲሻ ሻልልን ከጠየቅነው እጅግ ያነሰ እና ስብዕናን የሚጎዳ ነው ያሉት ደግሞ የደብረማርቆሰ መምህር ናቸው።ዶቼቬለ ለተነሳው ቅሬታ መልስ ለማግኘት የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴርን ፣የኢትዮጰያ ሲቪል ስርቪሰ ኮሚሺንና የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበርን ቢጠይቅም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆነ አካል ለጊዜው አላገኘም ።
ሀና ደምሴ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ