1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መረጋጋት የራቀው የአፍሪቃ ቀንድ ትኩሳቱ ጨምሯል

ሰኞ፣ ሐምሌ 8 2016

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ሳምንት ወደ ሱዳን አቅንተው ከሱዳን ብሔራዊ ጦር አዛዥ ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ጋር ተነጋግረዋል። የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ከዐቢይ አንድ ቀን አስቀድሞ ባለፈው ማክሰኞ ወደ ኤርትራ ተጉዘው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተዋል። በኬንያም የዊልያም ሩቶ መንግስት ተንገዳግዷል።

Infografik Number of BW soldiers abroad 2012

የአፍሪቃ ቀንድ አለመረጋጋት ወዴት ያመራ ይሆን ?

This browser does not support the audio element.

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ሳምንት ወደ ሱዳን አቅንተው ከሱዳን ብሔራዊ ጦር አዛዥ ጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን  ጋር ተነጋግረዋል። ዐቢይ በምስራቃዊ የወደብ ከተማዋ ፖርት ሱዳን ለሰዓታት የነበራቸውን ቆይታ ጽ/ቤታቸው «ለሱዳን መረጋጋት የሚያከናውኑት ጥረት ቀጣይ እርምጃ ነው» ብሎታል። የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ከዐቢይ አንድ ቀን አስቀድሞ ባለፈው ማክሰኞ ወደ ኤርትራ ተጉዘው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገናኝተዋል። የፕሬዚዳንት ሐሰን ሼህ መሐመድ ወደ አስመራ መጓዝ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ እሰጣገባ ውስጥ ከገቡ በኋላ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው።

በአፍሪቃ ቀንድ ሌላ ትኩሳት ይዞ የመጣው ኹነት በኬንያ በወጣቶች የተቀሰቀሰው አመጽ የቀላቀለ ተቃውሞ የፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶን መንግስት አንገዳግዷል። ፕሬዚዳንቱ አመጹን ለማርገብ የመንግስታቸውን ካቤኔ በይፋ በትነዋል። የኢትዮ ሶማሊያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻከር ገና ውሉ አልለየም ። ጂቡቲ እና ሶማሌላንድም መቆራቆስ ውስጥ ገብተዋል። ከውስጥም ከውጭም ጤና የራቀው የአፍሪቃ ቀንድ ትኩሳቱ ጨምሯል ።

የኃያላኑ ብሔራዊ ጥቅም መሳለጫ ፤ የአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ


ሃገራቱ በርስ በርስ ጦርነት እና ግጭት ይታወቃሉ ። በውስጥ የመልካም አስተዳደር ችግር ፣ ከጎሳ እና ከኃይማኖት ጋር የተያያዙ ፖለቲካዊ ቀውሶች ያስከተሏቸው ግጭት ጦርነቶችን ጨምሮ የኤኮኖሚ ችግሮች በመንግስታት ላይ አመጽ የቀላቀሉ ተቃውሞዎችንም እስከማስነሳት ደርሰዋል።  ግጭት፣ ጦርነት እና  አመጾቹ በርካታ ሺዎችን ለህልፈት ፤ ሌሎች በርካታ ሺዎችን ለአካል ጉዳት ዳርገው ሚሊዮኖችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎባቸዋል። በደሃ አቅማቸው ያፈሯቸው በቢሊዮን  ዶላሮች የሚገመቱ ሃብት ንብረታቸውም ለውድመት ተዳርጎባቸዋል። 


በዚህም አላበቃ፣ ተፈጥሮም ብትሆን  አልራራችላቸውም ፤ አንዴ በአንበጣ መንጋ ፣ ሌላ ጊዜ ብርቱ ድርቅ ባስከተለው የረሃብ አለንጋ ስትገርፋቸው ፤ ደስ ሲላት  መልኳን ቀየር አድርጋ ሊቋቋሙት የማይችሉትን ጎርፍ ትልክባቸዋለች። ሰውና እንስሳን ሳይለይ ከነመኖሪያ ሰፈራቸው ስንቶቹን ጠራርጎ ወስዷቸዋል ። ይህ የአፍሪቃ ቀንድ ነው። ድንበር ያልለያቸው ግን ደግሞ ግብራቸው ያመሳሰላቸው ጦረኛ ፣ ድሃ እና በስደት የሚታወቁ ህዝቦች መኖሪያ ። 

ማሕደረ ዜና፤ የኢትዮ-ሶማሊያ ዉዝግብ፣ የአፍሪቃ ቀንድ ተጨማሪ ሥጋት


ከታመመ የሰነበተው የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ባለፈው ሳምንት ትኩሳቱ ጨምሮ ነበር። ከሱዳን እስከ ጂቡቲ ፤ ከኢትዮጵያ እስከ ኬንያ ከሶማሊያ እስከ ኤርትራ ብዙ አነጋጋሪ ጉዳዮችንም አስተናግዷል። 
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ወደ ፖርት ሱዳን ከተማ አቅንተው ከሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና ከብሄራዊ ጦር አዛዥ ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ተነጋግረዋል። ዐቢይ ወደ ሱዳን የመጓዛቸው ዜና የተሰማው ዓመት ከመንፈቅ ሊደርስ የተቃረበው የሀገሪቱ ደም አፋሳሽ የእርስ በእርስ ጦርነት ሁሉን አቀፍ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለማበጀት የአፍሪቃ ህብረት ጥረት እያደረገ በነበረበት ወቅት ነው ። የጠቅላይ ሚንስትሩ በፖርት ሱዳን መገኘት እና ከብሄራዊ ጦሩ መሪ ጋር መነጋገር ለጊዜው በይፋ የተባለ ነገር ባይኖርም መሪዎቹ በጋራ ችግኝ ሲተክሉ የሚያሳዩ ምስሎች በይፋ ተለቀዋል። አቶ ዩሱፍ ያሲን የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮችን በቅርበት ይከታተላሉ ። ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ  በሱዳን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ያደረጉትን ጉዞ በቀጣናው የሚታይ ትኩስ እንቅስቃሴ አካል አድርገው ነው የሚመለከቱት ። 

ፎቶ ማህደር ፤ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ/ም ወደ ፖርት ሱዳን ከተማ አቅንተው ከሱዳን ሉአላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና ከብሄራዊ ጦር አዛዥ ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ጋር ተነጋግረዋል።ምስል Tony Karumba/AFP

የአፍሪካ ቀንድ ቀጣና የክረምት ወራት የዓየር ጠባይ ትንበያ


«የሱዳን ብቻ ሳይሆን በአካባቢው ብዙ እንቅስቃሴዎችን እናያለን ። እንቅስቃሴዎቹ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ነው የሚያሳዩን ። በየቦታውኮ በዚህ አካባቢ ችግር አለ። በሱዳን ችግር አለ፤ በሶማሊያ ችግር አለ። ባህር ተሻግረን በየመን ችግር አለ። በየቦታው ያው እሳት አለ»
ዐቢይ ወደ ሱዳን ባሄዱበት ወቅት የአፍሪቃ ህብረት እና  የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ጎን ለጎን በሱዳን ሰላም ለማስፈን በካይሮ እና አዲስ አበባ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ ቆይተዋል። በንግግሮቹ የተገኙ ውጤቶች ይፋ ሳይደረጉ ግን ሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ከፍተኛ ልዑካን ከመንግስታቱ ድርጅት ልዑካን ጋር ለመነጋገር ጄኔቫ መግባታቸው ተዘግቧል። እንዲያም ሆኖ ከሁለቱ ተፋላሚ ኃይላት አንደኛቸው ከመንግሥታቱ ድርጅት የሱዳን ልዩ መልእከተኛ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ አለመሆናቸው ነው የተነገረው። የመነጋገር ፍቃደኝነትን የነየበርበራ ወደብ፦ የኢትዮጵያ ወቅታዊ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴና የአፍሪቃው ቀንድሳው የትኛው ወገን እንደሆነ ግን ለጊዜው የተባለ ነገር የለም። 


በካይሮ ፣ በአዲስ አበባ ቀጥሎ በጄኔቫ ያልሰመረው ተፋላሚ ኃይላቱን የማቀራረብ ጥረት ወዴት እንደሚያመራ መገመት አስቸጋሪ ነው ። ይህ ከሆነ ታዲያ በእርግጥ አቢይ ወደ ሱዳን ተጉዘው ከአልቡርሃን ጋር ስለምን ተነጋግረው ይሆን ? በርካታ ጉዳዮች በመላ ምት ደረጃ ሊነሱ እንደሚችሉ የሚናገሩት አቶ ዩሱፍ ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ የራሳቸውን ስም ለማደስ ብሎም ሀገሪቱን ሊያሰጋት በሚችሉ  ጉዳዮች ላይ ሊያተኩሩ እንደሚችሉ ግን ይገምታሉ።
« የሚሰጡ በርካታ ግምቶች አሉ። ለሱዳን የርስ በርስ ጦርነት መፍትሄ ማፈላለጉ ፣ በሱዳን ጉዳይ የሃሜቲ ኃይሎች አዲሳባ እንዲሰባሰቡ መደረጉ ምክንያት ፤ መጀመሪያ ላይ ጦርነቱ ሲነሳ አብይ አህመድ ሱዳን ውስጥ ለሱዳን ችግር አለማቀፍ የሰላም አስከባሪ ይግባ ማለቱ ከአልቡርሃን ጋር በጣም አቀያይሟቸዋል። እና እዚያ ውስጥም የለሁም ለማለት ይመስላል፤ የሱዳን ጦርነት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እየተጠጋ መሄዱ እና በአማራ ክልል ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነትም ምክንያት ሊሆን ይችላል።»

በካይሮ ፣ በአዲስ አበባ ቀጥሎ በጄኔቫ ያልሰመረው ተፋላሚ ኃይላቱን የማቀራረብ ጥረት ወዴት እንደሚያመራ መገመት አስቸጋሪ ነው ። ምስል AFP

የበርበራ ወደብ፦ የኢትዮጵያ ወቅታዊ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴና የአፍሪቃው ቀንድ


የሱዳን የርስ በርስ ጦርነት ከመርገብ ይልቅ መባባሱ በገሃድ እየታየ ነው ። የብሔራዊ ጦሩ ደህንነት ባለፈው አርብ ባወጣው መግለጫ በመዲናዪቱ ካርቱም እና አጎራባች ግዛቶች የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል። ለዚህም የሁለት ሳምንት ያህል ጊዜ መስጠታቸውን የመገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ከዚህ በመነሳትም መዲናዪቱን ካርቱምን ጨምሮ አጎራባች አካባቢዎች ሌላ ቀውስ እና እልቂት እንደተደገሰላቸው መገመት አያዳግትም።
 ካለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር ጀምሮ በጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን በሚመራው የሱዳን ብሔራዊ ጦር እና በጄነራል ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄሜቲ በሚመራው የፈጥኖ ደራሽ ኃይል ወይም አር ኤስ ኤፍ መካከል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሀገሪቱ በታሪኳ አይታው በማታውቀው ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። ዕልቂት ፤ መፈናቀል እና ረሃብም የሱዳናውያን መለያ ሆኗል። 

ትኩረት በአፍሪቃ፤ የሱዳን ዉጊያ፣የአፍሪቃ ቀንድ ቀዉስ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ባለፈው ሳምንት ወደ ኤርትራ ተጉዘዋል ። በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑ ነው ። ይህም ዐቢይ ወደ ሱዳን ከማምራታቸው አንድ ቀን አስቀድሞ በዕለተ ማክሰኞ የተደረገ ይፋዊ ጉብኝት ነበር ።
 በተመሳሳይ ሳምንት ሶማሌላንድ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን «ለስልጠና» ወደ ኢትዮጵያ መላኳን አስታውቃለች። ኢትዮጵያ  ከሶማሌላንድ ጋር የወደብ እና የባህር ኃይል የጦር ሰፈር የሚያስገኝላትን ስምምነት ከተፈራረመች ወዲህ ከሶማሊያ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውጥረቱ አይሏል። ውጥረቱ እንዲረግብ የአፍሪቃ ኅብረት እና ምዕራባውያኑን ጨምሮ «የተረጋጉ» ማሳሰቢያዎች ሲሰጥበት ቢሰነብትም መፍትሄ አላስገኘም።ቱርክ ሁለቱን ሃገራት ለማሸማገል ያደረገችው ጥረትም ፍሬ አላፈራም። ሶማሊያ እንደ ግዛቴ ናት ከምትላት ሶማሌ ላንድ ጋር የተደረገውን ስምምነት ሉዓላዊነቷን እንደተዳፈረ ቆጥራለች። ይሁንና ኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት እና የባህር ኃይል የማደራጀት ፍላጎቷን በሶማሌላንድ በኩል ለማሳካት ከመረጠችው መንገድ ማፈግፈግ የፈለገች አትመስልም። የሰሞኑ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት  የሐሰን ሼህ መሐሙድ ወደ ኤርትራ መጓዝ እና ኢትዮጵያ የሶማሌላንድን ወታደሮች ለማሰልጠን መቀበል አንድ ነገር ግልጽ እያደረገ የመጣም መስሏል ። 

የሰሞኑ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት  የሐሰን ሼህ መሐሙድ ወደ ኤርትራ መጓዝ እና ኢትዮጵያ የሶማሌላንድን ወታደሮች ለማሰልጠን መቀበል አንድ ነገር ግልጽ እያደረገ የመጣም መስሏል ። ምስል REUTERS


የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ጉዳዮችን በመተንተን የሚታወቁት አቶ አብዱራህማን ሰኢድ እንደሚሉት ኢትዮጵያ የሶማሊያን የግዛት አንድነት የማያስከብር ፖሊሲ ይዛ እስከቀጠለች ድረስ  ሌላ ድንበር ተሻጋሪ ጦርነት ሊከሰት የሚችልበት ዕድሉ ሰፊ ነው። 
 
« ወደ ጦርነት አዝማሚያ የሚወስድ መሆኑ እየታየ ነው። እንዳልኩት በፖሊሲ ደረጃ የሶማሌን ግዛት የማያስከብር ፖሊሲ መከተል ጀምረዋል። ይሄ በአንጻሩ የሶማሌ መንግስትም ተመሳሳይ ፖሊሲ ልከተል ቢል እና ከሶማሌ ክልል ጋር የተለየ ግንኙነት ቢያደርግ ምን አይነት ቀውስ ሊፈጥር እንደሚችል መገመት ነው።»
ዶ/ር በለጠ በላቸው በአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ላይ ጥናቶች ሰርተዋል። ጉዳዩን በተለየ መንገድ ይመለከቱታል። ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሆኑ በሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ መካረር ውስጥ ሚና ያላቸው ሃገራት ወደ ጦርነት እንዲያመሩ የሚፈቅድላቸው ሁኔታ ውስጥ አይደሉም ይላሉ።

ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ሆኑ በሁለቱ ሃገራት ዲፕሎማሲያዊ መካረር ውስጥ ሚና ያላቸው ሃገራት ወደ ጦርነት እንዲያመሩ የሚፈቅድላቸው ሁኔታ ውስጥ አይደሉም ፤ ተንታኝምስል Eshete Bekele/DW

የሱዳን ውጊያ ምን ያክል ብርቱ ነው? የአፍሪቃ ቀንድን ምን ያክል ያሰጋል?

«እንደሱ ይሆናል ብዬ አልጠብቅም ። ለምን ለየትኛውም የቀጣናው ሀገር በተናጥልም ሆነ በጋራ አዋች አይደለም። እነኚህ ሁሉ መንግስታት በውስጥ ችግሮቻቸው በከፍተኛ ሁኔታ የተፈተኑ ናቸው ። ብዙዎቹ ኢኮኖሚያቸው ለችግር የተጋለጠ ነው። በውስጥ ችግሮቻቸው ምክንያት፤ ይህንን የውስጥ ድክመታቸውን ይዘው ከሌላ ሀገር ጋር ወደ ግጭት ያመራሉ ተብሎ አይታሰብም»
በአካባቢው ድንበር ተሻጋሪ ጦርነት የመቀስቀስ ዕድሉን አሳንሰው የሚመለከቱት ዶ/ር በለጠ ምንም እንኳ የአፍሪቃ ቀንድ አካባቢ ፈጣን እና ተለዋዋጭ ፖለቲካዊ አንድምታዎችን እያስመለከተ ቢሆንም በተቀረው ዓለም እየሆነ ካለው ማህበረ ፖለቲካ፣ ኤኮኖሚ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙት ጋር ያያይዙታል።


« በአፍሪቃ ቀንድ ላይ እጅግ በጣም የሚለዋወጥ የፖለቲካ ምህዳር እያስተዋልን መጥተናል። ይሄ በአፍሪቃ ቀንድ ብቻ ሳይሆን በተቀረው የዓለም ክፍል ላይም የሚታይ ነው። ለአፍሪቃ ቀንድ ብቻ የመጣ ነው ተብሎ በተናጥል የሚታይ አይደለም። በተቀረው የዓለም ክፍልም እንደአፍሪቃ ቀንድ ውስብስብ እና ወደ ግጭት ያመራ ባይሆንም ተመሳሳይ በሆኑ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ እንደገቡ መመልከት ይቻላል። »
ጦርነት ሊነሳ የሚችልበት ዕድሉ ኖረም አልኖረ በገሃድ የሚታይ አንድ እውነታ ግን አለ።  የኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ ወታደራዊ ትብብር ማሳያ የሚሆን ኢትዮጵያ ወደ አምስት ሺ የሚጠጉ የሶማሌ ላንድ  ወታደሮችን ለማሰልጠን ተቀብላለች። የሶማሌላንድ አስተዳደርም ወታደሮቹን መላኩን አረጋግጧል። ሶማሊያ በበኩሏ ለዓመታት ኤርትራ ውስጥ ስልጠና ሲወስዱ የነበሩትን ወታደሮቿን ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ ጥረቷን አጠናክራ ቀጥላለች። በሌላ በኩል ሶማሊያ በአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ጥላ ስር ከአስር ዓመታት በላይ ከአልሸባብ ጋር ሲዋጉ የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መጠየቋ ተዘግቧል። እንቅስቃሴዎቹ ሁሉ ግን እንዲሁ በችልታ የሚታዩ ጉዳዮች እንዳልሆኑም ነው ተንታኞቹ የሚናገሩት ። ምናልባትም ውጥረቱን ወደ ሌላ ምዕራፍ ሊበአፍሪቃ ቀንድ ለሚደጋገመው ድርቅ መፍትሄያሸጋግሩ ይችሉ እንደሆነ ይሰጋሉ ። 

የአፍሪቃን ቀንድ ህመም ያባባሰው እና ምናልባትም ሌላ የደህንነት ስጋት ይዞ የመጣው የኬንያ ወጣቶች በፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ መንግስት ላይ አመጽ የቀላቀለ ተቃዉሞ መቀስቀሳቸው ነው።ምስል TONY KARUMBA/AFP

በአፍሪቃው ቀንድ ድርቅ ለምን ይደጋገማል?
የአፍሪቃን ቀንድ ህመም ያባባሰው እና ምናልባትም ሌላ የደህንነት ስጋት ይዞ የመጣው የኬንያ ወጣቶች በፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ መንግስት ላይ አመጽ የቀላቀለ ተቃዉሞ መቀስቀሳቸው ነው። መንግስት ተጨማሪ ታክስ ለመጣል የሚያስችለውን ሕግ ተግባራዊ ለማድረግ በተነሳ ጊዜ በቁጣ የተነሱት ኬንያውያን ወጣቶች ፕሬዚዳንቱ ካቢኔያቸውን በትነው ከጥቂት ሰው ጋር እስኪቀሩ አድርሷቸዋል። መዲናዪቱ ናይሮቢን ጨምሮ በአንዳንድ የሀገሪቱ ከተሞች አመጹ አይሎም ለበርካታ ወጣቶች ህልፈት ምክንያት እስከ መሆንም አድርሶታል። ዶ/ር በለጠ እንደሚሉት ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ምክትል ፕሬዚዳንት በነበሩበት ዘመን የጠለሸ ስማቸውን ለማደስ እና ከምዕራባዊያን የተሻለ ተቀባይነት ለማግኘት ሲሉ የሀገር ውስጡን ድጋፍ ያጡበት ነው።


የኬንያው አመጽ የቀላቀለ ተቃውሞ አዲሱን የታክስ ረቂቅ ህግ አስቀርቶ ፣ ሚንስትሮችን አስበትኖ የሀገሪቱን ፖሊስ ከስራ አስለቅቆም የቆመ አይመስልም ። ፕሬዚዳንቱ ለምርጫ ቅስቀሳ የገቡትን ቃል አልፈጸሙም የሚሉት ተቃዋሚዎች በፕሬዚዳንቱ ላይ ያስነሱትን ተቃዉሞ አጠናክረው መቀጠላቸው እየታየ ነው። የሀገሪቱ ፖሊስ አመጹን ለመቆጣጠር ያልተመጣጠነ ኃይል እየተጠቀመ ነው የሚል ክስ የፖሊስን እርምጃ የሚከታተለው አይፒኤል ኦ የተሰኘ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድን አስታውቋል።

የኬንያው አመጽ የቀላቀለ ተቃውሞ አዲሱን የታክስ ረቂቅ ህግ አስቀርቶ ፣ ሚንስትሮችን አስበትኖ የሀገሪቱን ፖሊስ ከስራ አስለቅቆም የቆመ አይመስልም ። ምስል Daniel Irungu/EPA

ትናንት እሁድ ከመዲናዪቱ በስተደቡብ የተሰማው ዜና ደግሞ ነገሮች መስመር እየለቀቁ መሆናቸውን አመላክቷል። በቆሻሻ መጣያ ስፍራ የተቆራረጡ የስምንት ሰዎች አስክሬን መገኘቱ ለኬንያ እና ኬንያውያን ብቻ ሳይሆን የተቀረውንም ዓለም ጉድ አስብሏል። የተሻለ መረጋጋት እና ለተቀረው የአፍሪቃ ክፍል የተሻለ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር እንዳላት የሚነገርላት ኬንያ በእርግጥ መታመሟን አሳይቷየአፍሪቃ ኅብረት ነጻ የንግድ ቀጣና እና ሌሎችም ጉዳዮችል። 

የአፍሪቃ ኅብረት ነጻ የንግድ ቀጣና እና ሌሎችም ጉዳዮች
የዴሞክራሲ ተምሳሌት ነኝ የምትለው  አሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንቷ በምርጫ ዘመቻ ላይ እያሉ ከተቃጣባቸው የግድያ ሙከራ በተዓምር ተርፈዋል። ዴሞክራሲን ተንከባክቤ አሳደኩ የምትለው ሀገር ያስተናገደችው አስደንጋጭ ክስተት የሀገሪቱን ፖለቲካ ለዘልዓለሙ ቀይሮታል።  ሩስያ እና ዩክሬን የገቡበት ጦርነት ሩስያ እና የምዕራቡን ዓለም ዓይን እና ናጫ አድርጓል ፤  የመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ከራቀው ሰነበተ ። የኮሪያ ልሳነ ምድርም ውጥረት አይሎበታል። በዚህ ሁሉ መሃል ግን በድህነት ፣ ድርቅ ፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ እና በውስጣዊ የፖለቲካ ሽኩቻ የሚናጠው እና ብሎም የእርስ በርስ ጦርነት የሚደቀው የአፍሪቃ ቀንድ የራሱን ችግር በራሱ የመፍታት ተስፋው ለጊዜው አይታይም ። በራሱ ጉዳይ የተያዘውን የተቀረውን ዓለም ትኩረት በሚገባው መጠን ምን ያህል  ሊያገኝ ይችል ይሆንም? ያጠያይቃል። 
ታምራት ዲንሳ 
ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW