1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መራሂተ መንግስት አንገላ ማርክል የሮማዉን ዻዻስ ጉብኝት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 24 1998

የሮማዉ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ሊቀ ሊቃነ ዻዻሳት ቤኔዲክት 16ኛ የግል እንግዳቸዉን መራሂተ መንግስት አንገላ ማርክልን ለመጀመርያ ግዜ በበጋዉ ማረፍያቸዉ Castello Gandolfo ተቀብለዉ አስተናግደዋል።

አንገላ ማርክል የሮማዉ ዻዻስ ጋር በእንግድነት
አንገላ ማርክል የሮማዉ ዻዻስ ጋር በእንግድነትምስል AP

ሰኞ 22.12.98 ዓ.ም ሁለቱ ባለሥልጣናት በግል ጉዳዮች ባይነጋገሩም በተለይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በሚገኘዉ የመካከለኛዉ ምስራቅ ሁኔታና ጀርመን በመጭዉ የፈረንጆቹ አመት የአዉሮፓዉ ህብረት ርእስነት ስትረከብ በሚኖራት ሚና ተወያይተዋል።
መራሂት መንግስት አንገላ ማርክል የአዉሮፓዉ ህገመንግስት ዉል እግዚአብሄር ከሃሊነት እንዲጠቀስበት እንደሚፈልጉ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን ርዕሰ ለቀ-ሊቃነ-ዻዻሳት ቤኔዲክት 16ኛ በግል በጎበኙዋቸዉ ግዜ ለጀርመን ጋዜጠኞች ገልጸዋል። የክርስትና ሃይማኞት ለአዉሮፓ ባህል መሰረት ነዉ ሲሉም ገልጸዋል። በመጭዉ የፈረንጆቹ አመት ጀርመን የአዉሮፓዉን ህብረት በመሪነት ለስድስት ወራት ታገለግላለች። በመጀመርያም የአዉሮፓ ህብረት ህገመንግስት ረቂቅ እምነት በተመለከተ ምንም ነገር እንዳይጻፍ ሲል በፈረንሳይ እና በኒዘርላንድ የተሰበሰበዉ የድምጽ መሰብሰብያ ሰንጠረዥ በመግለጹ የቫቲካኑ መንግስት ድርጊቱን በተደጋጋሚ ነቅፎት እንደነበር የሚታወስ ነዉ። መርሃኢተ መንግስቷ፣ አዉሮፓ፣ በህገ መንግስቱ ዉል እግዚያብሄርን ያማከለ ማንነቱን የሚያሳይ መስተዳድር ያስፈልጋታል ባይ ናቸዉ ። በነፍሻማዉ አልባና የባህር ዳርቻ ከሚገኘዉ ቤኔዲክት 16ኛ የበጋ ማረፍያ ስፍራ አንገላ ማርክል ጥሩ አየር ሲያጋጥማቸዉ አብረዋቸዉ ላሉት እንግዶች እምነት ለሳቸዉ አስፈላጊ እና ተቀዳሚ እንደሆነ በተደጋጋሚ በግልጽ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል።
«እኔ የምጸልየዉ፣ ምንም እንኳ ሰዎች፣ ስህተት ብንሰራም ከእግዚያብሄር እርቀን፣ እንዳንገኝ ነዉ። የሰዉን ልጆች ልዩ መሆንን እና ክብራቸዉን የሚያዉቅ እሱ ነዉ። ስለሆነም ለኛ ለክርስትያኖች፣ ለኔ፣ ሃይማኞት በጣም አስፈላጊ ነዉ።»
ሊቀ-ሊቃነ ዻዻሳት ቤኔዲክት 16ኛ መራሂተ መንግስት አንገላ ማርክልን በእንግድነት ከታቀደዉ ሰአት በላይ ነበር ያስተናገዱት። ሁለት ሳምንት በማይሞላ ግዜ ዉስጥም ሊቀ ሊቃነ ዻዻሱ በጀርመን በባቫርያ ግዛት እንደሚመጡ ይጠበቃል። ቤኔዲክት 16ኛ በመጭዉ ጀርመን ጉብኝታቸዉ ስለሃይማኖት፣ ዉጥረት እናም ግጭትን በተመለከተ በሚነሳዉ እርዕስ ላይ እንደሚያተኩሩ በተለይ ለጀርመኗ መሪ ለአንጌላ ማርክል ጠቃሚ እንደሚሆን ይታመናል።የመነጋገርያቸዉ እርዕስ በተለይም በሊባኖስ የወደፊት ጉዳይ ላይ እንደሚያተኩር ታዉቋል። የቫቲካን ድፕሎማሲያዊ ጥረትም ከብዙ ግዚያት በከፍተኛ ልምድ በኻላ በአለማችን ዙርያ ተፈላጊ እንደሚሆንም ይታመናል።
እንዲህ አይነቱ የሁለትዮሽ መንግስታዊ ጉብኝት በሮማዉ ቤተ-ክርስትያን ያልተለመደ ሲሆን፣ ከአርባ ደቂቃዎች ቆይታ በኻላ የጀርመኗ መሪ አንገላ ማርክል Ciampino ከተሰኘዉ የሮማዉ የጦር ሰራዊት አዉሮፕላን ማረፍያ ጉዞአቸዉን ቀጥለዋል። አንጌላ ማርክል ሊቀ-ሊቃነ ዻዻሳት ቤኔዲክት 16ኛን ጎበኙበት ወቅት የፖለቲካ አማካርያቸዉ Chirstop Hausgen አብረዋቸዉ እንደነበሩም ታዉቋል።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW