1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መርካቶ-አዲስ አበባ ዉስጥ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ ብዙ ንብረት አወደመ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 12 2017

አካባቢዉን ዛሬ ጠዋት የተመለከተዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ስዩም ጌቱ እንደዘገበዉ የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች እሳቱን ለማጥፋት እስከ ማርፈጃዉ ድረስ ሲታገሉ ነበር።ራሳቸዉን የአካባቢዉ ባለሥልጣናት እንደሆኑ የገለፁ ሰዎች ግን ጋጤኛዉ ሥለቃጠሎዉ ያሰባሰበዉን መረጃ በሙሉ ደምስሰዉበታል

ትናንት አዲስ አበባ መርካቶ የተነሳዉን ቃጠሎ ለመታዘብና ለመዘገብ የተጓዘዉ ባልደረባችን የሰበሰበዉን መረጃ ባለሥልጣናት ቀምተዉታል
አዲስ አበባ ዉስጥ ከቅርብ ዓመታት ወዲሕ በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሳ የእሳት ቃጠለ በሚሊዮን ብር የሚቆጠርጥፋት ያደርሳልምስል Yared Shumete

መርካቶ-አዲስ አበባ ዉስጥ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ ብዙ ንብረት አወደመ

This browser does not support the audio element.

 

አዲስ አበባ ዉስጥ መርካቶ የገበያ ሥፍራ ትናንት ማታ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ በርካታ መደብሮች አጋየ።ሸማ ተራ በተለዉ የገበያ ማዕከል በተለይም አንድ ሕንፃ ላይ የተነሳዉ ቃጠሎ እስከ ዛሬ ጠዋት ድረስ ሳይጠፋ ቀጥሎ ነበር።አካባቢዉን ዛሬ ጠዋት የተመለከተዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ስዩም ጌቱ እንደዘገበዉ የእሳት አደጋ መከላከያ ሠራተኞች እሳቱን ለማጥፋት እስከ ማርፈጃዉ ድረስ ሲታገሉ ነበር።ራሳቸዉን የአካባቢዉ ባለሥልጣናት እንደሆኑ የገለፁ ሰዎች ግን ጋጤኛዉ ሥለቃጠሎዉ ያሰባሰበዉን መረጃ በሙሉ ደምስሰዉበታል።በባለሥልጣናቱ አፈና ምክንያት የተሟላ ዘገባ ማቅረብ አልቻልንም።ይሁንና ቃጠሎዉ ያደረሰዉን ጉዳትና የባለሥልጣናቱን የኃይል እርምጃ በተመለከተ ስዩምን ባጭሩ አነጋግሬዋለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW