1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መስቀል በትግራይ-በሰላምና በልዩነት መሐል

ሐሙስ፣ መስከረም 17 2016

በተለይም በመቐለ፣ ዓዲግራት፣ ኢሮብ አካባቢዎች የተለየ ድባብ ያለው ሲሆን የዘንድሮው በዓል በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች በድምቀት በጎዳናዎች እንዲሁም ሌሎች ህዝብ የሚሰበሰብባቸው ቦታዎች እየተከበረ ያለው ለሶስት ዓመት በጦርነቱ ምክንያት ተስተጓጉሎ ከቆየ በኃላ ነው

Äthiopien Tigray Meskel
ምስል Million Haileslasse/DW

ትግራይ ዉስጥ መስቀል በአደባባይ ሲከበር በ3 ዓመት ዉስጥ የመጀመሪያዉ ነዉ

This browser does not support the audio element.

 

ፖለቲከኞች ሲታረቁ፣ የሐይማኖት መሪዎች በተለያዩባት ትግራይክልል የመስቀል በዓል ከሶስት ዓመት በኃላ በተለየ ድምቀት በአደባባዮች ተከብሮ ውሏል። በመቐለ ጮምዓ ተራራ የዘንድሮው የመስቀል በዓል በቀድሞ ድምቀቱ የተከበረ ሲሆን በአዲግራት ጨምሮ በተለያዩ ከተሞችም እንዲሁም ልዩ የበዓል ድባብ ተስተውሏል።የእየሱስ ክርስቶስ መስቀል የተገኘበት ተብሎ በኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው ዓመታዊው የመስቀል በዓል በዚህ በትግራይም በተለየ ትውፊት፣ በባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ስነስርዓት ከዋዜማው መስከረም 16 እስከ በዓሉ ዕለት መስከረም 17 ተከብሮ ይውላል። መስቀል  በተለይም በመቐለ፣ ዓዲግራት፣ ኢሮብ አካባቢዎች የተለየ ድባብ ያለው ሲሆን የዘንድሮው በዓል በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች በድምቀት በጎዳናዎች እንዲሁም ሌሎች ህዝብ የሚሰበሰብባቸው ቦታዎች እየተከበረ ያለው ለሶስት ዓመት በጦርነቱ ምክንያት ተስተጓጉሎ ከቆየ በኃላ ነው።

የመስቀል በአል አከባበር በመቀሌምስል Million Haileslasse/DW

በመቐለመስቀል ሲከበር ከሌላው የተለየ ጥንታዊ ስነስርዓት አለው። ህዝብ በብዛት በመቐለ ወደሚገኘው ጮምዓ የተባለ ግዙፍ ተራራ ይወጣል፣ በተራራው ጫፍ ላይ ደመራ ይለኮሳል፣ ወጣቶች ችቦ ይዘው እየጨፈሩ፣ ዚግዛግ እየሰሩ ወደከተማው መሃል ይገባሉ።ይህ ባህላዊ ስነስርዓት ከጥንት ጀምሮ የነበረ መሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች እና ሀገር ሽማግሌዎች ይገልፃሉ። ትላንት በጮምዓ ተራራ በነበረ ስነስርዓት አግኝተን ያነጋገርናቸው በዕድሜ የገፉት ወይዘሮ ሕይወት መሰለ "ድሮ እኛ ሳንወለድ ጀምሮ መስቀል በመቐለ በጮምዓ ተራራ ጫፍ ይከበር ነበር" ይላሉ።

የጮምዓ ስነስርዓት

የመቐለ የመስቀል ጮምዓ ስነስርዓት በተለይም የቀድሞ የትግራይ አስተዳደር ራእሲ መንገሻ ስዩም ወደ ተራራው መውጫ መንገድ ከሰሩለት በኃላ የተለየ ድባብ ይዞ እየቀጠለ ስለመሆኑም ይገለፃል።የወጣቶች ባህላዊ ጨዋታ፣ የልጃገረዶች ጭፈራ፣ የሃይማኖት ስነስርዓት፣ የፖሊስ እና ወጣቶች ፍጥጫ በየዓመቱ በጮምዓ የሚታዩ ትእይንቶች ናቸው።

የመስቀል በዓል የሚከበርበት የጮምዓ ጉብታምስል Million Haileslasse/DW

በዓሉ ሲያከብሩ ያገኘናቸው አማኑኤል ገብረእግዚአብሔር የዘንድሮው የመስቀል በዓል ካለፊት ዓመታት በተሻለ ድባብ በአደባባይ ማክበር መቻላቸው ደስታ ፈጥሮላቸዋል።ከመቐለው የጮምዓ ተራራ የመስቀል በዓል አከባበር በተጨማሪ በትግራይ ክልል በዓዲግራት፣ ማይጨው፣ጥንታዊቷ አክሱም ከተማ እና ሌሎች የዘንድሮው በዓል ከሶስት ዓመት በኃላ በአደባባይ በድምቀት ተከብሯል።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

ዮሐንስ ገብረእግዜአብሔር 

 

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW