መስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተከበረ
ሐሙስ፣ መስከረም 16 2017ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተከበረ። የሃይማኖቱ ምዕመን ከእኩለ ቀን ጀምሮ በምልዐት በመስቀል አደባባይ በመገኘት የሚያከብረው ይህ የደመራ ሥነ ሥርዓት ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች በሕብር የሚታየበት መሆኑ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ቤተ ክርስትያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ርእሠ ብሔር ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ በሥነ ሥርዓቱ ላይ የታደሙ ሲሆን ሚኒስትሮች እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በተወካያቸው በኩል በሥነ ሥርዓቱ ላይ ታድመዋል። አዲስ አበባ ላይ የሚገኘዉን ወኪላችንን ሰለሞን ሙጬን ከበዓሉ ሥፍራ በስልክ አነጋግረነዋል።
ሠለሞን ሙጬ
አዜብ ታደሰ
ታምራት ዲንሳ