መቅዲሹ፤ የተመድ ከፍተኛ ርዳታ ለሶማሊያ ጠየቀ
ማክሰኞ፣ የካቲት 28 2009ማስታወቂያ
የማዳኑ ዕድል መኖሩን በመጠቆምም ዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ ከሰባት ዓመት በፊት የተከሰተዉ እንዳይደገም ባፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ ጥሪ አስተላልፈዋል። ሶማሊያ በ25 ዓመታት ጊዜ ዉስጥ ለሦስተኛ ጊዜ በድርቅ የተመታች ሲሆን የዛሬ ሰባት ዓመት የተከሰተዉ ድርቅ 260 ሺህ ሰዎችን መፍጀቱን የፈረንሳይ የዜና ወኪል አመልክቷል። ጉተሬዥ በመቃዲሾ ቆይታቸዉም አዲስ ከተመረጡት የሀገሪቱ ፕሬዝደንት መሐመድ አብደላ መሐመድ ጋር ተነጋግረዋል። ሶማሊያ የብዙዎች ድጋፍ እንዳላቸዉ የሚነገርላቸዉ ፕሬዝደንት መሐመድ ከተመረጡ ወዲህ ወደመረጋጋት እያመራች ነዉ ቢባልም ድርቁ የከፋ ርሃብ ያስከትላል የሚል ስጋት አለ። አንድ ሀገር ከጠቅላላ ህዝቧ 20 በመቶዉ ምግብ የማግኘት ዕድል ከሌለዉ በይፋ ለርሃብ መጋለጡ ይታወጃል። ሶማሊያ በአሁኑ ይዞታዋ 5,5 ሚሊየን የሚሆን ሕዝቧ በድርቁ ምክንያት በተከሰተዉ የዉኃ እጥረት ለዉኃ ወለድ በሽታዎች ተጋልጧል። የተመድ ሶማሊያን ጨምሮ በድርቅ ለተጎዱ አራት የአፍሪቃ ሃገራት 4,4 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልገዉ አመልክቷል። ድርጅቱ እንደሚለዉ በእነዚህ ሃገራት በጠቅላላዉ ከ20 ሚሊየን የሚበልጡ ሰዎች ለከፋ ርሃብ ተጋልጠዋል።