መቐለን ጨምሮ በትግራይ ከተሞች የተስፋፋዉ ወንጀል አሳሳቢ ሆንዋል ተባለ
ሰኞ፣ ነሐሴ 12 2017
በትግራይ በተለይም ከጦርነቱ በኃላ በከተሞች በርካታ ወንጀሎች እየተፈፀሙ መሆኑ በነዋሪዎች የሚገለፅ ሲሆን በነዚህ ወንጀሎች በርካቶች ሞተዋል፣ እገታ እና ዝርፍ መበራከቱ ይገለፃል። በዚህ ሳምንት እንኳን በመቐለ ከስራው ወደቤቱ ሲመለስ የነበረው ወጣት ድንገት መጥፋቱ በበርካቶች ዘንድ ቁጣ እንዲሁም ስጋት የፈጠረ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም የአክሱም ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህር እና ተመራማሪ በድንገተኛ ሁኔታ መገደላቸው ተነግሯል። እነዚህ ወንጀሎች በፖሊስ ክትትል እየተደረገባቸው ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ የተለያዩ ከተሞች በህፃናት እና ሴቶች ጨምሮ በበርካቶች ላይ ዝርፍያ እና ፆታዊ ጥቃት ዓለማ ያደረጉ በርካታ ወንጀሎች ይፈፀማሉ። እነዚህ ወንጀሎች ነዋሪዎች አማረው ይገኛሉ። በትግራይ የጋዜጠኞች መታገት
በክልሉ በአጠቃላይ በተለይም ደግሞ በትላልቅ ከተሞች በትጥቅና እና ተሽከርካሪዎች የተደገፈ ዝርፍያ፣ በህፃናት እና ሴቶች ጨምሮ በተለያዩ ነዋሪዎች የሚፈፀም እገታ ብሎም ግድያ፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲሁም ሌሎች እየተፈፀሙ እንዳለ የክልሉ አስተዳደር ጭምር ይገልፃል። በቅርቡ በድንገት በሚደረጉ ፍተሻዎች ሕገወጥ የጦር መሳርያዎች፣ ለወንጀል ተግባራት የሚውሉ ስለቶች እና ሌሎች መሳርያዎች መያዙ የሚገልፀው የትግራይ ፖሊስ ኮምሽን ወንጀሎች ለመከላከል እየሰራ ቢሆንም አሁንም ግድያ ጨምሮ ሌሎች ተግባራት መቀጠላቸው ይገልፃል። የትግራይ ፖሊስ ኮምሽን ምክትል ኮምሽነር ጌታቸው ኪሮስወንጀል ለመከላከል እየሰራን ቢሆንም አሁንም ግድያ አለ፣ የግድያ ሙከራ ይፈፀማል፣ ንጥቅያ አለ። ወንጀል ሙሉበሙሉ ማስቆም ባይቻልም ስጋት የሚያስወገድ ማድረግ ይገባል። ህዝብ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ መስራይ ይጠበቅብናል" ብለዋል። በቅርቡ የሚከበሩ በዓላት ተከትሎ እንግዶች ወደመቐለ በብዛት ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የተናገሩት የፖሊስ አዛዡ ጥበቃ ይደረጋል ስጋት አይግባችሁ ሲሉ ተደምጠዋል።
ሚሊዮን ኃይለሥላሴ
አዜብ ታደሰ
ታምራት ዲንሳ