«መንግሥታዊ ሌብነት የለም» ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ
ሐሙስ፣ ሰኔ 27 2016
ኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት አይሳካም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናገሩ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በስም እና የት እንደተደረገ ባይጠቅሱም በኢትዮጵያ መንፈቅለ መንግስት ለማድረግ ውይይት የሚያደርጉ አካላት መኖራቸውን ጠቅሰው እሳቤው የማይሳካ መሆኑን ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ባልታጠቁ ዜጎች ላይ "የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል" በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ መንግሥት "በጅምላ አልገደለም"፣ የሚፈፀሙ ጥፋቶችን ለማረም መንግሥታቸው እንደሚሠራ ተናግረዋል። ጦርነትና ግጭት እንዲቆም አሁንም የመንግሥት ፍላጎት መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ችግሮችን በንግግር እና ውይይት ለመፍታት ዝግጁ መሆናቸውንም አመልክተዋል።የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ« የሕግ መርሆዎችን የሚጥስ ነው» መባሉ
16 የምክር ቤት አባላት ላቀረቡላቸው ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ "ኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት አይሳካም" ያሉ ሲሆን፣ መንግስት መሰል ጥረት እንዳይሳካ አድርጎ ተቋማትን መገንባቱን ገልፀዋል። ይህንን እሳቤ ያራመዱት እነማን እንደሆኑ እና የት ሆነው እንደመከሩ ግን አልገለፁም።
ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በብዙ የአማራ ክልል ከተሞች ባልታጠቁ ዜጎች ላይ የጅምላ ግድያ ተፈጽሟል፣ መንግሥት የሕሊና እሥረኞችን ለመፍታት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማቆም ምን ወስኗል የሚል ጥያቄም ቀርቦ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥታቸው ጅምላ ግድያ እንዳልፈፀመ ገልፀዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ሰበብ በማድረግ የመንግስት ኃይሎች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽመዋል የሚልም ጥያቄ ቀርቦ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሰብዓዊ መብት ተሟጋችነት ስም የተቋቋሙት ያሏቸው ድርጅቶች አሰራራቸውን ሊፈትሹ ይገባል ሲሉ መልሰዋል።የህወሓትን ሕጋዊ ሰውነት ሊመልስ የሚችል ሕግ ፀደቀ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአማራም ሆነ በኦሮሚያ ክልሎች ያሉት ዋና ችግሮች "ዱር ግባ" የሚል ኃይለኛና የራቀ ያሉት ፕሮፖጋንዳ እንዲሁም ይህንን ሰምቶ "ጥራኝ ዱሩ" ብሎ ወደጫካ የሚገባ ኃይል መኖሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
"በብሔር በሽታ የተጠመደ እኛን በብሔር ይከሰናል" ያሉት ዐቢይ መንግሥታቸው ትጥቅ ካነሱት ጋር ለመነጋገር እና ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል። ከሌላ የምክር ቤት አባል "የመንግሥት መዋቅር በሌቦች ተጥልፋል" ይህ ለምን የሚል ጥያቄም ቀርቦላቸው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሉ አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ« የሕግ መርሆዎችን የሚጥስ ነው» መባሉ
"በሶማሊያ የግዛት አንድነት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ምንም ጥያቄ የለውም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት ከሁሉም ጎረቤት ሀገራት ጋር በትብብር ከመሥራት እና የባሕር በር ከማግኘት ውጪ ሌላ ግብ እንደሌለው ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢኮኖሚ፣ በማሕበራዊ እና ሌሎች ጉዳዮች ላይም ሰፌ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በዚህም ኢኮኖሚያዊ ዕድገት መኖሩን፣ የሀገሪቱ ዕዳ ወደ 17.5 መውረዱን፣ ኮንትሮባንድ፣ ገቢ ስወራ እና የንግድ ማጭበርበር የሀገር ውስጥ ገቢ የመሰብሰብ አቅምን ማዳከሙን፣ በዚህ ዓመት 7.9 በመቶ የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲሚጠበቅ መገመቱን ገልፀዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ