1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

መንግሥት "በሚፈልገው ልክ" የምርጫ በጀት እንደፈቀደለት ምርጫ ቦርድ ገለፀ

ሰኞ፣ ሐምሌ 14 2017

"ቦርዱ እንደ አዲስ ይዋቀር? እሱን ቦርዱን የሚያዋቅረው አካል የሚሰጠው መልስ ነው። እኛ እስከምናውቀው ድረስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ላለፉት ስድስት ዓመታት በገለልተኝነት ሲሠራ እንደነበረው አሁንም ቀጥሎ በገለልተኝነት እየሠራ ያለ ተቋም ነው"።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ
የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ኃይሉምስል፦ Ethiopian Broadcasting Corporation

መንግሥት "በሚፈልገው ልክ" የምርጫ በጀት እንደፈቀደለት ምርጫ ቦርድ ገለፀ

This browser does not support the audio element.

መንግሥት "በሚፈልገው ልክ" የምርጫ በጀት እንደፈቀደለት ምርጫ ቦርድ ገለፀ

በቀጣዩ ዓመት ለሚያከናውነው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ "በሚፈልገው ልክ እና ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል" ያለው በጀት ከመንግሥት እንደተፈቀደለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ የቦርዱን በጀት በተመለከተ ዶቼ ቬለ ላቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ቦርዱ ለ2018 መደበኛ እና ለምርጫ ሁለት የበጀት ጥያቄዎችን አቅርቦ "በሚፈልገው ልክ" ተፈቅዶለታል ብለዋል።

ምርጫውን ለማከናወን "በመንግሥት በኩል ከፍተኛ ቁርጠኝነት አለ" ያሉት ሰብሳቢዋ ይህንኑ ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ከሳምንታት በፊትበሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ካፀደቀው የ2018 ጠቅላላ በጀት ውስጥ የመደበኛ ወጪ ዝርዝርን በሚጠቅሰው ክፍል ውስጥ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት 10.85 ቢሊዮን ብር መመደቡ ሰፍሯል። ይህም ለመከላከያ እንዲሁም ለፍትሕና ደህንነት ተቋማት ከተመደቡ ከፍተኛ መጠን ያለቸው የበጀት ወጪ ድልድሎች ቀጥሎ የሚቀመጥ ነው። 

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላተ ወርቅ ኃይሉ ላለፉት ስድስት ዓመታት ያገለገለውንና በቅርቡ ማሻሻያ የተደረገበትን የምርጫ እና የፓርቲዎችን ጉዳይ የሚመራውን አዋጅ አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት ማብራርያ የተቋሙን በጀት በተመለከተ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ቁጥር ባይገልፁም ቦርዱ ሥራውን ለማከናወን የሚያስችለው በጀት እንደተፈቀለት መልሰዋል።

ሰብሳቢዋ የፖለቲካ እና የሲቪክ ምህዳር የመጥበብ ሥጋት መኖሩ በሚመለከታቸው አካላት እንደሚነሳ ተጠቅሶ ለቀረበላቸው ጥያቆም ተቋማቸው የመፍትሔ አካል ለመሆን በየዕለቱ አስፈላጊ ክትትል እንደሚያደርግ ተናግረዋል። በትግራይ ክልል የሚኖራውን የምርጫ ዝግጅት ኹኔታም ምላሽ ሰጥተውበታል።

"በየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ምርጫ ለማድረግ ዝግጅት እንደምናደርግም፣ ይህንኑ ምርጫ በትግራይም [7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ] ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነን"።

"በየትኛውም የሀገሪቱ ክልል ምርጫ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነን"ምስል፦ Shewangizaw Wegayehu/DW

ትናንት መግለጫ ያወጣውኦፌኮ "የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የሕዝብን አመኔታ እንዲያገኝ በሁሉም ፓርቲዎች ሙሉ ስምምነት ላይ ተመስርቶ በአዲስ መልክ እንዲዋቀር" ሲል በቀጣዩ ምርጫ ለመሳተፍ ይህንን እንደ አንድ ቅድመ ሁኔታ አድርጎ አቅርቧል። በዚህ እና በቦርዱ ላይ ለተነሳው የገለልተኝነት ጥያቄ ሰብሳቢዋ ምላሽ እንዲሠጡ ጠይቀናቸው ነበር።

"ቦርዱ እንደ አዲስ ይዋቀር? እሱን ቦርዱን የሚያዋቅረው አካል የሚሰጠው መልስ ነው። እኛ እስከምናውቀው ድረስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ላለፉት ስድስት ዓመታት በገለልተኝነት ሲሠራ እንደነበረው አሁንም ቀጥሎ በገለልተኝነት እየሠራ ያለ ተቋም ነው"።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተከናወነ 10 ዓመታት ያለፉትን የአካባቢ ምርጫ ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በኋላ ሊያከናውን እንደሚችል ተስፋውን ገልጿል። በሌላ በኩል ምንም እንኳን ሕዝብና ቤት ቆጠራ ከተከናወነ ዓመታት ቢቆጠሩም ቦርዱ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሲያከናውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ስንት ነው በሚል ነው ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ መነሻ የሚያደርጉት ባለፈው ምርጫ የነበረውን የመራጮች ቁጥር እንደሆነና ከዚያ ላይ በመነሳት አማካይ ቁጥር ታሳቢ እያደረጉ እንደሚሆን ጠቅሰዋል።
ሰሎሙን ሙጬ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW