1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግሥት በሰሜን ተራሮች ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ   

ሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2011

መንግስት  የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እየደረሰ ያለውን ጥፋት ፈጥኖ እንዲያቆም የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ ተካሄደ።  ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በፓርኩ ላይ እሳት የሚለኩሱ አካላት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡

Demo in der Region Debark, weil die Regierung zögert, während der Nationalpark Simen brennt
ምስል DW/A. Mekonnen

ለፓርኩ ትኩረት ይስጥ፣ ዩኔስኮ የራሱን ድርሻ ይወጣ

This browser does not support the audio element.


በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተቀጣጠለው እሳት አስካሁንም ሙሉ በሙሉ መጥፋት እንዳልቻለ ከስፍራዉ የደረሰን ዜና ያመለክታል። እሳቱን ለማጥፋት የተለያዩ ጥረቶች ቢደረጉም በተለይ በቆላማው አካባቢ የሚገኘዉ ፓርክ ዉስጥ ቃጠሎ እስካሁንም እንዳልጠፋ የአካባቢ ነዋሪዎች ገልፀዋል። መንግሥት ቃጠሎዉን ለማጥፋት ትኩረቱን እንዲሰጥ በደባርቅ ከተማ ላይ Simen mountain Ethiopia የተካሄደዉ ሰላማዊ ሰልፍ አንዱ መገለጫ ነው ተብሎአል። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከተነሱ  መልዕክቶች መካከል መንግስት ለፓርኩ ትኩረት ይስጥ፣ ዩኔስኮ የራሱን ድርሻ ይወጣ፣ የፓርኩ ባለቤትነት ለክልሉ መንግስት ይመለስ የሚሉ እንደሚገኙበት ወታት በሰረት ተናግሯል፡ የሰሜ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች አስተባባሪ አቶ ፋንታዬ ጥላሁን ኅብረተሰቡ ያነሳውን  ጠያቄ ለሚመለከተው የመንግስት አካል እንደሚደርሱ ጠቁመው ኅብረተሰቡ በፓርኩ ህልውና ላይ የተደቀነውን አደጋ መንግስትና ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ተረባርበው እንዲስወግዱ የሚጠይቅ ሰልፍ መካሄዱን አረጋግጠዋለወ፡፡ የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የህብረተሰብና ቱሪዝም ሀብት ኃላፊ አቶ ታደሰ ግዛው አንደሚሉት በደጋማው አካባቢ ያለዉ እሳት ጠፍቷል፡፡ በሥራ ላይ አስካሁን አንድ የእሳት መጥፊ አውሮፕላን ተሰማርቶአልም ብለዋል። እስካሁን  400 ሄክታር የደኑ ክፍል በእሳቱ መዉደሙም ታዉቋል። 220 ኪሎሜትር ካሬ ስፋት ያለው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ እ . ኤ. አ በ1969 የተመሰረተ ሲሆን በ1978 ደግሞ በተባበሩት መንግስታት የትምህረት፣ሳይንስና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበ ነው፡፡ 

ዓለምነው መኮንን


አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ   
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW