1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መንግሥት በአማሮች ላይ የሚደርሰዉን እንግልትና መዋከብ እንዲያስቆ መጠየቁ

ሰኞ፣ መጋቢት 25 2015

በአማራ ክልል ሁለት ከተሞች በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች መንግሥት በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ የሚደረጉ እንግልቶችና መዋከቦችን እንዲያስቆም ተጠይቋል፣ በወፍላና ወፍላ ከተሞች ደግም መንግሥት የአማራ ማንነት ጥያቄያችን በአስቸኳይ ይመልስ የሚል ሰለፍ በኮረም ከተማ ተካሂዷል፡፡

Äthiopien Bahir Dar | Friedlicher Protest gegen Premierminister Abiy
ምስል Alemenew Mekonnen/DW

 በአማራ ላይ የሚደርሰዉን እንግፍ እና እንግልት መንግሥት ያስቁምልን

This browser does not support the audio element.

 በአማራ ክልል ሁለት ከተሞች በተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች መንግስት በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ የሚደረጉ እንግልቶችና መዋከቦችን እንዲያስቆም ተጠይቋል፣ በወፍላና ወፍላ ከተሞች ደግም መንግስት የአማራ ማንነት ጥያቄያችን በአስቸኳይ ይመልስ የሚል ሰለፍ በኮረም ከተማ ተካሂዷል፡፡
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ደንበጫና ጂጋ ከተሞች ላይ በተካሄዱት የተቃዎሞ ሰልፎች ከአማራ ክልል ውጪ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የሚደረገው ወከባ እንዲቆም የሚጠየቁ መልዕክቶችም በሰልፎቹ እንደተላለፉ ላይ አስተተያየት ሰጪዎቹ አመልክተዋል፣ በፖለቲካ ምክንያት የታሰሩ እንዲፈቱም ተጠይቋል፡፡
በደንበጫ ከተማ በተካሄደው ሰልፍ ላይ ከተገኙት የሰልፉ ተሳታፊዎች መካከል አንዱ በሰልፉ የተንፀባረቁ መልዕክቶችን ዘርዝረዋል፡፡
“ከአማራ ክልል ውጪ የሚኖሩ አማራዎች፣ በተለይ በኦሮሚያ፣ በአዲስ አበባ፣ አሁን ሸገር በተባለው አካባቢ ብሔራቸውን መሰረት ያደረገ ጥቃት እተፈፀመባቸው ነው”
አስተያየት ሰጪው ጨምረው እንዳመለከቱት፣ በፖለቲካ ሰበብ የታሰሩ ወገኖች ከእስራት እንዲፈቱ ሰልፈኞቹ መጠየቃቸውን ገልጠዋል፡፡ በዚሁ ዞን በጂጋ ከተማ የተካሄደውን ሰልፍ በማስመልከትም አንድ የሰልፉ ተሳታፊ መፈናቀሎች በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደረገው እስራት እንዲቆም፣ እንዲሁም የኑሮ ውድነት በዝቅተኛ ነዋሪው ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠረ በመሆኑ የገበያ መረጋጋት እንዲፈጠር መንግስትን መጠየቃቸውን ለዶይቼ ተናግረዋል፡፡
የአማራና የትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱባቸው የኮረም ከተማ አስተዳደር፣ የዛታና ወፍላ ወረዳዎች ነዋሪዎችም መንግስት የአማራ ማንነት ጥያቂያችንን በአስቸኳይ ያረጋግጥልን በሚል ሰልፎች ትናንት ማካሄዳቸውን አንድ የሰልፉ ተሳታፊ ለዶይቼ ቬሌ አመልክተዋል፡፡
በሌላ በኩል ትናንት በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ከለውጡ ወዲህ የተመዘገቡ ድሎችን የሚያወድሱ እነዚሁ ድሎችን ለማስቀጠል የተባሉና መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች መካሄዳቸው ይታወሳል፡፡

በአማራክ ክልል የተካሄደዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ምስል Alemenew Mekonnen/DW


ዓለምነው መኮንን

አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ከ DW