1. ወደ ይዘቱ እለፍ
  2. ወደ ዋናዉ ገጽ እለፍ
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ እለፍ

መንግሥት ዝቅተኛ የሠራተኞች የደሞዝ ወለልን ተግባራዊ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ሰለሞን ሙጬ
ዓርብ፣ ሐምሌ 11 2017

የኢትዮጵያ መንግሥት የሠራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እርከንን በሕግ ተግባራዊ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሲየሽን ጠየቀ። ይህ ባለመሆኑ ሠራተኞች ሕይወታቸውን ለመምራት የማያግዝ ዝቅተኛ ደሞዝ እንዲከፈላቸው ከማደረጉም በላይ፣ ለሥራ ማጣት ሥጋትም እንዳጋለጡ ማድረጉ ተገልጿል።

22ኛው ዙር  የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሲየሽን ዓለም አቀፍ ጉባኤ
22ኛው ዙር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሲየሽን ዓለም አቀፍ ጉባኤ ምስል፦ Solomon Muchie/DW

መንግሥት ዝቅተኛ የሠራተኞች የደሞዝ ወለልን ተግባራዊ እንዲያደርግ ተጠየቀ

This browser does not support the audio element.

መንግሥት የሠራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለልን ተግባራዊ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሲየሽን ጠየቀ

የኢትዮጵያ መንግሥት የሠራተኞች ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል እርከንን በሕግ ተግባራዊ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሲየሽን ጠየቀ። ይህ ባለመሆኑ ሠራተኞች ሕይወታቸውን ለመምራት የማያግዝ ዝቅተኛ ደሞዝ እንዲከፈላቸው ከማደረጉም በላይ፣ ለሥራ ማጣት ሥጋትም እንዳጋለጡ ማድረጉ ተገልጿል። ማሕበሩ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በሚመለከት ዛሬ ባካሄደው 22ኛው ዙር ዓለም አቀፍ ጉባኤ ሀገሪቱ "ጦርነት ኢኮኖሚዋን እየበላው ነው" የሚል ሀሳብ ተንፀባርቋል። መንግሥት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ "ተዐምራዊ" በሚባል ደረጃ መሻሻል ማሳየቱን ደጋግሞ ቢገልጽም ባለሙያዎች ግን "ወደ ሕዝቡ ኪስ ውስጥ የገባ ዕድገት የለም" በሚል ይከራከራሉ።

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት (ILO) አባል ሀገር ናት። 90 በመቶ የዚህ ድርጅቶች አባል ሀገራት ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ደንግገው የአነስተኛ ደሞዝ ተከፋዩን ዜጋ ኑሮ ለማሻሻል ጥረት ያደርጋሉ። ኢትዮጵያ ግን እስካሁን ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል የላትም። በየዓመቱ 2 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊ ወጣት ሥራ አጥ እንደሚሆን የገለፁት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሲየሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አዲስ ካሳሁን የዋጋ ግሽበት፣ ተደራራቢ ግብር ከመንግሥት ውጪ የሚቀጠረውን ሠራተኛ አኗኗር ፈታኝ አድርጎታል ብለዋል።“አዲሱ የደመወዝ ገቢ ግብር ረቂቅ የኑሮ ጫናን ያገናዝብ” የሰራተኞች ኮንፌዴሬሽን

"የኢትዮጵያ ንግድ አሁን የሕልውና ኹኔታ ላይ ነው ያለው። ዕድገት ላይ አይደለንም። ሲከብደን [የግል ቀጣሪ ድርጅቶች] ሠራተኛ እናባርራለን። ለሠራተኛው በጣም አስቸጋሪ የሆነ ወቅት ላይ ነው ያለነው"። የሠራተኛ እና ክህሎት ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሷል። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ "ተዓምራዊ" በሚባል ደረጃ እያደገ መሆኑ ተደጋግሞ በመንግሥት በኩል ተገልጿል። የኢኮኖሚ ባለሙያው ዶክተር አጥላው አለሙ ግን ይህንን አይቀበሉትም።

ኢሰማኮ ሀገር አቀፍ የስራ ማቆም እንደሚጠራ አስጠነቀቀ"ዕድገቱ በጣም ተፈናጥሯል የሚለው ነገር እኔ አይመስለኝም። አድጓልም ከተባለ የት ነው ያለው? የት ነው የገባው የሚለው ነገር ይመጣል። አድጎ ሊሆን ይችላል። ግን ወደ ሕዝቡ ኪስ ውስጥ ግን አልገባም"። ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል ለመወሰን የኢኮኖሚ ኹኔታውና የሠራተኞችን ፋላጎት ማጣጣም እንደሚገባ፣ የጠራ የሕዝብም ሆነ የገቢ እና የክፍያ መረጃ እንደሚያስፈልግ፣ ኢ-መደበኛውን የሥራ ዘርፍ መደበኛ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሲየሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር አዲስ ካሳሁን የመንግሥት የኢኮኖሚ ማሻሻያ ግን በጦርነት እየተበላ መሆኑን ገልፀዋል። "መንግሥት ሪፎርም ያደረገው ተገቢ የፖሊሲ አቅጣጫ ነው። ነገር ግን ሰላም እና ደህንነት ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአሁኑ ጊዜ የጦርነት ኢኮኖሚ ነው"።

22ኛው ዙር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚክ አሶሲየሽን ዓለም አቀፍ ጉባኤ ምስል፦ Solomon Muchie/DW

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) ሰሞኑን የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በሚመለከት ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት የመንግሥት ድጎማ መነሳት፣ የግብር ሥርዓቱ መሻሻል፣ የገንዘብ ፓሊሲዉ መጠናከር፣ የዋጋ ንረት መቀነስን በዓወንታ ጠቅሷል። ሆኖም የፀጥታ ችግር እና የግጭት ሥጋት፣ የለጋሽ ሀገራት ድጋፍ መቀነስ፣ በጥቁር ገበያ እና በመደበኛው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ያለው ልዩነተ እንደገና እየሰፋ መምጣት፣ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት እንደተጠበቀው አለመሆኑን ጠቅሶ የኢኮኖሚ ማሻሻያው እንዳይደናቀፍ ሥጋቱን ገልጿል። ዶክተር አጥላው አለሙም ይህንን ይጋራሉ። የደሞዝ ጭማሪው «ሳይመጣ የሄደ ተስፋ» ወይስ ደጓሚ ?የሠራተኞች ማሕበራት በገቢ ግብር ማሻሻያ ዙሪያ ለመንግሥት ጠንካራ መከራከሪያ አቀረቡ

"ዘለን የውጭ ምንዛሪ ሥርዓቱን ነጻ ማድረግ አደጋ ያለው ነው። የትይዩ እና የመደበኛ የምንዛሪ ግብይቱን ማቀራረብ አልቻልንም። የትኛውን እያመረትን ነው የምንሸጠው? ቋሚ የሆነ የዶላር ምንጭ አለን ወይ ነው ጥያቄው"። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከመንግሥት ሠራተኞች ግብር የማይከፈልበት ዝቅተኛ የደሞዝ መጠን ከ8300 ብር ያላነሰ እንዲሆን በሠራተኞች ማህበራት ውትወታ ቢደረግበትም ትናንት 2000 ብር አድርጎ አጽድቆታል። የመንግሥት ሠራተኞች ኑሮ ከብዷቸዋል፣ ወደ ልመና እየወጡ ነው፣ መንግሥት ለዚህ አጣዳፊ ጉዳይ አሳማኝ መፍትሔ ይስጥ የሚለው ተደጋጋሚ ጥሪም ተቀባይነት አላገኘም።

ሰለሞን ሙጬ

 አዜብ ታደሰ

 ማንተጋፍቶት ስለሺ 

 

ቀጣዩን ክፍል እለፈው የ DW ታላቅ ዘገባ

የ DW ታላቅ ዘገባ

ቀጣዩን ክፍል እለፈው ተጨማሪ መረጃ ከ DW

ተጨማሪ መረጃ ከ DW